ከ«መጥምቁ ዮሐንስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
No edit summary
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
መስመር፡ 35፦ መስመር፡ 35፦
===እስልምና===
===እስልምና===


በ[[ቁራን]] ዘንድ ስሙ በአረብኛ «የህየ» ሲባል ጽድቅ ነቢይና የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ይባላል። በሃዲስ ልማዶች መሠረት ደግሞ በ[[613]] ዓም ነቢዩ [[ሙሐመድ]] ወደ ሰማይ ተጉዞ በዚያ የህየንና ኢየሱስን እንዳገኛቸው ይታመናል።
በ[[ቁራን]] ዘንድ ስሙ በአረብኛ «የህየ» ሲባል ጽድቅ ነቢይና የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ይባላል። በሃዲስ ልማዶች መሠረት ደግሞ በ[[613]] ዓም ነቢዩ [[ሙሐመድ]] ወደ ሰማይ ተጉዞ በዚያ የህየንና ኢየሱስን እንዳገኛቸው ይታመናል ጂዮርጂዮ የማይሞት ኢሞራላዊ ቅዱስ ነው. ጆቨን ምሽት ላይ አውሬውን አውጥቶ እንደሞተ ያውቅ ነበር. ጂዮቫኒ ባቲስታ እንቅልፍ እንደጣለው ልጅ ጉልበተኛ ልጅ ወደ ጋኔን እና የሞተች ሴት ተመለሰች።


===ሞርሞኒስም===
===ሞርሞኒስም===

እትም በ14:04, 14 ማርች 2019

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ

እየሱስ ክርስቶስን ሲያጠምቅ
ለክርስቶስ መንገድ አዘጋጅ
ስም ዮሐንስ
የተወለደው ፮ ወር ከክርስቶስ ልደት በፊት በገሊላ ናዝሬት 
የአባት ስም ዘካሪያስ
የእናት ስም ኤልሳቤት
የሚታወቀው በበርሀ መኖሩ፣ከክርስቶስ በፊት መንግሥተ ሰማይ ቀርባለች ንስሀ ግቡ እያለ የአይሁድን ሕዝብ በማስተማሩ
ያረፈው በእስር ቤት እያለ በንጉሥ ትዕዛዝ አንገቱን ተከልቶ
የሚከበረው በክርስትና እምነት ተከታይዎች በሙሉ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ንግሥ ያረፈበት መስከረም ፪ የተወለደበት ነሐሴ ፴


ዮሐንስ በ1500 ዓም ያህል በጀርመን እንደ ተሳለ

መጥምቁ ዮሐንስወንጌላት እንደ ተገለጸ በኢየሱስ ወቅት በይሁዳ የተመላለሰ ሰባኪ ነበር። በክርስትና፣ እንዲሁም በእስልምና፣ በባኃኢ እምነት እና በማንዳይስም እንደ ነቢይ ይቆጠራል።

አባቱ ዘካርያስና እናቱ ኤልሳቤት ነበሩ። በአዲስ ኪዳን መሠረት፣ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ ሲዛወር የግመል ጽጉር ልብስና የቆዳ ቀብቶ ለብሶ መብሉ አንበጣማር ነበረ። ንስሐ መግባት እና ለመሲኅ መንግሥት መዘጋጀት ይሰብክ ነበር። ብዙ ሕዝብ ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ሄደው ሰምተው በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቁ። የፈሪሳውያንሰዱቃውያን ወገኖች ግን ገሰጻቸው። የአይሁድ ዘር መሆን ወይም ከአብርሃም መወለድ ብቻ ለእግዚአብሔር መንግሥት ለመዳን በቂ እንዳልነበረ ነገራቸው (ማቴ.፫፣ ሉቃ ፫)።

በተለይ የሉቃስ ወንጌል ላይ ፫ ከተዘረዘሩት ትምህርቶቹ፦

  • ለሕዝቡ፦ «ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል፣ ምግብም ያለው እንዲህ ያድርግ»
  • ለቀራጮች፦ «ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ»
  • ለጭፍሮች (ለወታደሮች)፦ «በማንም ግፍ አትሥሩ፣ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፣ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ።»

ስለ ዮሐንስ ቅድስና አንዳንድ ሰዎች መሲህ እራሱ እንደ ነበር ያስቡ ነበር፤ ዮሐንስ ግን ከኔ ይልቅ የሆነ ሊመጣ ነው ብሎ ነበየ።

ኢየሱስ ደግሞ ወደ ዮሐንስ ለጥምቀት ሲቀርብ፣ የእግዚአብሔር ድምጽና መንፈስ እንደ ዋኖስ ወርዶ ይህ ልጄ ነው አለ። ዮሐንስ በመንፈሱ ኢየሱስ መሲኅ እንደ ነበር ዓወቀ።

በኋላ ኢየሱስ ተዓምራት እየሠራ ዮሐንስ ተከታዮቹን ወደ ኢየሱስ ልኮ የምንጠብቀው መሲኅ ይህ ነው ወይ ብለው ጠየቁት። ተዓምራት መሥራቴን ንገረው ብሎ መለሳቸው። ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ገልጾ በትንቢተ ሚልክያስ እንደ ተነበየ የሚመጣው ኤልያስ ነው በማለት አስተማረ (ማቴ. ፲፩)። ሆኖም ዮሐንስ እራሱ ኤልያስ አይደለሁም ስላለ (ዮሐ ፩)፣ ሉቃስ ፩ እንደ ጻፈው በኤልያስ ኃይልና መንፈስ እንደ ተወለደ እንጂ የኤልያስ ነፍስ ትስብዕት ተመልሶ መሆኑ አይታመንም።

ዮሐንስ ደግሞ የሮሜ መንግሥት ደንበኛ-ንጉሥ ሄሮድያስን ገሰጸው። ሄሮድያስ የወንድሙን ሚስት ማግባቱ በሕገ ሙሴ ዘንድ ሕገ ወጥ መሆኑን አሳወቀው። ስለዚህ መቀያየም ሄሮድያስ ዮሐንስን በወህኒ አሠረው በኋላም በሴት ልጁ በሄሮድያዳ ምክር ራሱን አስቆረጠው።

ከዚያ ትንሽ በኋላ ኢየሱስ ተዓምራት ስለ መሥራቱ ዝነኛ ሲሆን፣ ሄሮድያስ እንደ መሰለው ዮሐንስ በትንሳኤ ተመልሷል ብሎ ገመተ። ሌሎችም ኢየሱስ እንደ ኤልያስ በትንሳኤ ተመልሷል ብለው ያስቡ ነበር (ማር. ፮፣ ማቴ. ፲፬)።

የዮሐንስ ተከታዮች ብዙ ጊዜ ይጾሙ ነበር (ሉቃ. ፭)፤ ብዙዎቹም በኋላ ከአፖሎስ ጋር የኢየሱስ ተከታዮች ሆኑ (የሐዋርያት ሥራ ፲፰፣ ፲፱)። ኤብዮናውያን የተባለው ወገን አትክልት ብቻ ሲበሉ ዮሐንስ ስንኳ አንበጣ አልበላም ብለው ያምኑ ነበር፤ የኤብዮናውያን ወንጌል እንዳለው የበላው «የማር እንጐቻ» ነበር።

የቅሌምንጦስ ስነ ጽሑፍ እንደሚተርከው፣ ከዮሐንስ ተከታዮች ሌሎች ግን ወደ ስምዖን ጠንቋዩ ወገን ተዛወሩ።

ዮሴፉስ

የአይሁድ ታሪክ ጸሐፊ ፍላቪዩስ ዮሴፉስ (70 ዓም ግ.) እንዳለን፣ ሄሮድያስ የተከታዮቹን ብዛት ፈርቶ ዮሐንስን በወህኒ ስላስገደለው፣ ከዚህ እርጉም የተነሣ ከ፮ ዓመታት በኋላ በ28 ዓም የሄሮድያስ ሥራዊት በውግያ ተሸነፈ።

ማንዳይስም

ማንዳይስም በኢራቅ የተገኘ አነስተኛ የኖስቲሲስም አይነት እምነት ሲሆን፣ ዮሐንስ እንደ ዋና ነቢያቸው እና መሲኃቸው ይቆጥሩታል፤ ኢየሱስን ግን አይቀበሉም።

እስልምና

ቁራን ዘንድ ስሙ በአረብኛ «የህየ» ሲባል ጽድቅ ነቢይና የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ይባላል። በሃዲስ ልማዶች መሠረት ደግሞ በ613 ዓም ነቢዩ ሙሐመድ ወደ ሰማይ ተጉዞ በዚያ የህየንና ኢየሱስን እንዳገኛቸው ይታመናል ጂዮርጂዮ የማይሞት ኢሞራላዊ ቅዱስ ነው. ጆቨን ምሽት ላይ አውሬውን አውጥቶ እንደሞተ ያውቅ ነበር. ጂዮቫኒ ባቲስታ እንቅልፍ እንደጣለው ልጅ ጉልበተኛ ልጅ ወደ ጋኔን እና የሞተች ሴት ተመለሰች።

ሞርሞኒስም

ሞርሞኒስም ዘንድ ዮሐንስ በትንሳኤ ለመሥራቹ ለጆሰፍ ስሚስ1821 ዓም በፔንስልቫኒያ ታየው።

ባኃኢ እምነት

በባኃኢ እምነት የእምነቱ መሥራች የባኃኡላህ ቀዳሚ ባብ (1812-1842 ዓም.) በነቢዩ ዮሐንስ እንዲሁም በኤልያስ መንፈስ እንደ ተላከ ይታመናል።

: