ከ«ደብረ ዳሞ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
No edit summary
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ Advanced mobile edit
No edit summary
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ Advanced mobile edit
መስመር፡ 5፦ መስመር፡ 5፦
|ስዕልcaption = ደብረ ዳሞ ገዳም በጥንታዊ የህንጻ አሰራር ዘዴ
|ስዕልcaption = ደብረ ዳሞ ገዳም በጥንታዊ የህንጻ አሰራር ዘዴ
|አገር = [[ኢትዮጵያ]]
|አገር = [[ኢትዮጵያ]]
|ዓይነት =
|ዓይነት = አራት መዐዘን
|አካባቢ =
|አካባቢ = አዲግራት ፣ [[ትግራይ]]
|ዓመት =
|ዓመት = ፮ኛው ክፍለዘመን
|አደጋ =
|አደጋ =
|Extension =
|Extension =

እትም በ09:58, 26 ኦክቶበር 2019

ከአለት የተፈለፈለ
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
ደብረ ዳሞ

ደብረ ዳሞ ገዳም በጥንታዊ የህንጻ አሰራር ዘዴ
አገር ኢትዮጵያ
ሌላ ስም {{{ሌላ ስም}}}
ዓይነት አራት መዐዘን
አካባቢ** አዲግራት ፣ ትግራይ
የቅርስነት ታሪክ
ቅርሱ የተሰራበት ዘመን ፮ኛው ክፍለዘመን 
ደብረ ዳሞ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ደብረ ዳሞ
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ
* የአለበት ቦታ
** የዩ.ኔ.ስ.ኮ. ክልል ክፍፍል


ደብረ ዳሞ6ኛው ክፍለ ዘመን የተቆረቆረ ገዳምና ይህ ገዳም የሚኖርበት ተራራ ስም ነው። ደብረ ዳሞ ከአዲግራት በስተምዕራብ በመካከለኛው ትግራይ ይገኛል። ከተራራው ቀጥ ብሎ ለመውጣት አዳጋችነቱ የተነሳ ወደገዳሙ ለመድረስ ከቆዳ በተሰራ ገምድ ላይ መንጠላጠል ግድ ይላል። ቤተ ክርስቲያኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥንታዊ የአሰራር ዘዴን ተከተሎ እስካሁን ዘመን ድረስ በመዝለቅ ቀደምትነት ስፍራን ይይዛል ።

የተሰራውም በአቡነ አረጋዊ በ6ኛው ክፍለ ዘመን እንደነበር ትውፊት አለ። ቶማስ ፓከናም የተባለው የታሪክ ተመራማሪ አምባው እንደ ወህኒአምባ ግሸን ወንድ የነገስታት ዝርያወችን ለማሰሪያነት ያገለግል እንደነበር ትውፊት እንዳለ በጥናት ደርሶበታል። [1] የገዳሙ ውጫዊ ወለሎች በጥንቱ ዘመን ዘዴ፣ የኖራ ድንጋይንና የጥድ እንጨትን በማፈራረቅ የተሰራ ነበር። ይህም በስነ ህንጻ ጥበበ አክሱማዊ ዘዴ አሰራር ይባላል።[2]

እዚህ አምባ ላይ የሰውም ሆነ የእንስሳ ሴቶች መውጣት አጥብቆ የተከለከለ ነው። ሆኖም ግን በግራኝ አህመድ ወረራ ወቅት ንግስት ሰብለ ወንጌል እና ደንገጡሮቻ እዚህ አምባ ላይ በመጠለል ከሞት ድነዋል። ተራራው ላይ ምንጭና እህል የሚዘራበት ሰፊ መሬት ስለነበር ፖርቱጋሎቹ እነ ክሪስታቮ ደጋማ ከአምባው ደርሰው ንግስቲቱ እንድትወርድ እስከአሳመኗት ድረስ የግራኝን ሰራዊት ከዚህ አምባ ላይ ሆና መከላከል ችላለች።



ማጣቀሻ

References

  1. ^ Thomas Pakenham, The Mountains of Rasselas (New York: Reynal & Co., 1959), pp. 79-86
  2. ^ Pakenham, p. 85