ከ«ትርኪ ተራራ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
robot Modifying: en:Turkey Mountain inscriptions
robot Modifying: en:Turkey Mountain (Oklahoma)
መስመር፡ 12፦ መስመር፡ 12፦
[[Category:ተራሮች]]
[[Category:ተራሮች]]


[[en:Turkey Mountain inscriptions]]
[[en:Turkey Mountain (Oklahoma)]]

እትም በ06:46, 3 ኦክቶበር 2008

ትርኪ ተራራቱልሳ አካባቢ ኦክላሆማ ክፍላገር አሜሪካ ውስጥ ከአርካንሳው ወንዝ አጠገብ የሚገኝ ሲሆን እንዲያውም ተራራ ሳይሆን ትልቅ ኮረብታ ነው። በዚያ ላይ በተገኙት ድንጋዮች ላይ ያሉት ምልክቶች 'የጥንታዊ አሜሪካ መዝገቦች' ተብለዋል። በአንድ ዋሻ ውስጥ የተቀረጹት ስዕሎችና ምልክቶች ከውቅያኖስ ማዶ የመጡት መርከበኞች ሥራ መሆናቸውን አንዳንድ ምሁር ያምናል።

በዋሻው የሚታይ አንዱ ምልክት የላቲን አልፋቤት ፊደላት «PIA» ይመስላል። ከዚህ በላይ አንዳንድ መስመር ሊታይ ይችላል። አወዛጋቢው ምሁር ባሪ ፌል ይህን «PIA» የሚለውን ቃል ከ«A»-ኡ ቅርጽ የተነሣ እጅግ ጥንታዊ መሆኑን ገመተ። በሱ አስተሳሰብ በከነዓን ቋንቋ የተጻፈው 'ፓያ' ወይም 'ነጭ' ለማለት ነው። መስመሮቹ ደግሞ የኦጋም ፊደል መስለውት በጎይደሊክ ቋንቋ 'ጒን' ወይም 'ነጭ' እንደሚል ያምናል። በሁለት ቋንቋዎች የተጻፈ ቃል ማለቱ ይሆናል።

ይህ ሥፍራ ልክ በጋዲር ('የሄራክሌስ ዓምዶች' ወይም የዛሬው ካዲዝ) ኬክሮስ ላይ (36 N) ይገኛል። በመጽሐፈ ኩፋሌ መሠረት ከጋዲር ወደ ምዕራብ የሚሄድ መስመር የሞሳሕ ያፌት ርስት ከከነዓን ካም ርስት ይለያል።

የውጭ መያያዣዎች