ኤአናቱም

ከውክፔዲያ
የአሞራዎች ጽላት ክፍል

ኤአናቱም ከ2254 እስከ 2195 ዓክልበ. ድረስ ግድም የሱመር ከተማ ላጋሽ ንጉሥ ነበረ። አንድ ጽሑፍ እንደሚገልጸው ስሙ በሱመርኛ «ኤአናቱም» ሲሆን የቲድኑ (ሶርያ) ስያሜው «ሉማ» ነበረ። በርሱ መሪነት ላጋሽ ሰፊ ግዛት ይይዝ ነበር።

ኤአናቱም የአኩርጋል ልጅና ተከታይ ሲሆን የላጋሽ ንጉሥ ከሆነ በኋላ ሌሎቹን ከተሞች ለመያዝ ጀመረ። ኪሽን (ምናልባት ከንጉሡ ካልቡም) ጨመረ። በሐማዚ ንጉሥ ሀዳኒሽ ዘመን ደግሞ ትልቅ እንደ ነበር ይቻላል፤ በኋላ ዘመን በኒፑር መቅደስ «ሀዳኒሽና ሉማ» የተባሉ የአናብስት ሀውልቶች ነበሩ። በኡሩክ ንጉሥ ኤንሻኩሻና ዘመን ኤአናቱም በተለይ አሸናፊ ሆነ፤ የአክሻክ ንጉሥ ዙዙን ድል አደረገ፤ ከዚያ በኋላ ላርሳኡማዑር ከኤንሻኩሻና ያዘ። ከዚህ በላይ ኤአናቱም መንግሥቱን ወደ ስሜን እስከ ሹቡርና እስከ ማሪ ድረስ አስፋፋ፤ ኤላምንም ወረረ። በመጨረሻ በ2195 ዓክልበ. ግድም ኡሩክና ኒፑር ወድቀው ኤንሻኩሻናን ገለበጠው። ትንሽ ከዚህ በኋላ ግን ኤአናቱም ሞቶ ግዛቱ እንደገና በየከተማው ተከፋፈለ። ስለዚህ የኤንሻኩሻና ልጅ ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ የሱመር ላዐላይነቱን ከኡሩክና ኒፑር ያዘ። የኤአናቱም ወንድም ኤናናቱም የላጋሽ አለቃ ወይም ከንቲባ ሆነ።

ኤአናቱም በተለይ የሚታወቅበት «የአሞራዎች ጽላት» ስለሚባለው ቅርስ ነው። ይህ ትርዒት የኤአናቱም ድል በኡማ ንጉስ ኤናካሌ ላይ ለማስታወስ ተቀረጸ።

ቀዳሚው
አኩርጋል
ላጋሽ ገዥ
2254-2195 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኤናናቱም
ቀዳሚው
ኡሩክ ንጉሥ ኤንሻኩሻና
ሱመር አለቃ
2195 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
የኡሩክ ንጉሥ ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ