ኬንያ

ከውክፔዲያ

የኬንያ ሪፐብሊክ
Jamhuri ya Kenya (ስዋሂሊ)
(ጃምሁሪ ያ ኬኛ)

የኬንያ ሰንደቅ ዓላማ የኬንያ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር «ኤ ሙንጉ ንጉቩ ዬቱ» (ስዋሂሊ)
የኬንያመገኛ
የኬንያመገኛ
ኬንያ በአረንጓዴ ቀለም
ዋና ከተማ ናይሮቢ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ስዋሂሊ እና እንግሊዝኛ
መንግሥት

ፕሬዝዳንት
ምክትል ፕሬዝዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር
የከፊል ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ
ኡሁሩ ኬንያታ
ዊልየም ሩቶ
ዋና ቀናት
ታኅሣሥ ፪ ቀን ፲፱፻፶፮ ዓ.ም. (ዲሴምበር 12, 1963 እ.ኤ.አ.)
ታኅሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. (ዲሴምበር 12, 1964 እ.ኤ.አ.)
 
ነፃነት ከብሪታንያ

ሪፐብሊክ ታወጀ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
580,367 (47ኛ)
2.3
የሕዝብ ብዛት
የ2021 እ.ኤ.አ. ግምት
የነሐሴ 2019 ዓ.ም. ቆጠራ
 
54,985,698 (29ኛ)
47,564,296
ገንዘብ የኬንያ ሺሊንግ
ሰዓት ክልል UTC +3
የስልክ መግቢያ +254
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .ke

የኬንያ ሪፐብሊክ በምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በሰሜን ከኢትዮጵያ፣ በሰሜን-ምስራቅ ከሶማሊያ፣ በደቡብ ከታንዛኒያ፣ በምስራቅ ከዩጋንዳ፣ በስሜን-ምዕራብ ከደቡብ ሱዳን፣ በደቡብ-ምስራቅ ከሕንድ ውቅያኖስ ጋር ድንበር ትጋራለች።

አውሮፓውያን አካባቢውን ማሰስ የጀመሩት ከ፲፱ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሲሆን የብሪታንያ መንግሥት የምሥራቅ አፍሪካ ፕሮቴክቶሬትን በ1895 እ.ኤ.አ. አቋቁሟል። ይህ ፕሮቴክቶሬት በ1920 እ.ኤ.አ. የኬንያ ግዛት ተብሎ ተሰይሟል። ነፃ የኬንያ ሪፐብሊክ በዲሴምበር 1963 እ.ኤ.አ. ታወጀ።

የኬንያ ስም የመጣው በአፍሪካ በከፍታ ሁለተኛ ከሆነው ከደብረ ኬንያ ተራራ ነው። በዚሁ ተራራ ዙሪያ የሚኖሩት ነገዶች ስሙን «ኪኛ» (በካምባኛ)፣ «ኪሪማራ» (በአመሩኛ)፣ «ኪሬኛ» (በኤምቡኛ)፣ «ኪሪኛጋ» (በኪኩዩ)፣ ወይም «ኬሪ» (በመዓሳይኛ) ይሉታል። የነዚህ ስሞች ሁሉ ትርጉሞች «ቡራቡሬ» ሲሆኑ ይህም ደግሞ «ሰጎን» ማለት ነው፤ አመዳይ ያለበት የተራራው ጫፍ ለተመልካች ቡራቡሬ ወንድ ሰጎንን ያሳስባልና።

በኦገስት 2010 እ.ኤ.አ. በተካሄደ ውሳኔ ሕዝብ (referendum) መሠረት ከብሪታንያ የተወረሰው ሕገ መንግሥት በአዲስ ሕገ መንግሥት ተለውጧል። በአሁኑ ጊዜ ኬንያ በ፵፯ ካውንቲዎች (የአስተዳደር ክፍሎች) ተዋቅራለች። እነዚህ ካውንቲዎች በሕዝብ በተመረጡ ሰዎች የሚስተዳደሩ ሲሆን በናይሮቢ ከሚገኘው ማዕከላዊ መንግሥት በነፃነት ይንቀሳቀሳሉ።

የኬንያ ዋና ከተማ እና ትልቋ ከተማ ናይሮቢ ናት። የኬንያ ኢኮኖሚ በምሥራቅና መካከለኛው አፍሪቃ በጂ.ዲ.ፒ. (GDP) ትልቁ ነው። ግብርና በአገሪቱ ትልቅ የሥራ ዘርፍ ሲሆን ከኤክስፖርቶች መካከል ሻይቡና እና ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ አበባዎች ይገኛሉ። እንዲሁም ቱሪስምፔትሮሊየም አቢይ ዘርፎች ናቸው።