Jump to content

አንድምታ

ከውክፔዲያ

አንድምታ የሚለው ቃል «አንድም» ከሚለው የአማርኛ ቃል የመጣ ሲሆን የአረፍተ ነገሮችን ድብቅ ትርጉም አውጥቶ ለማሳየት የሚረዳ ቃል ነው። አንድምታ ((እንግሊዝኛ)exegesis) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ውስጥ የመጽሃፍ ቅዱስን ትርጉም ለማወቅ የሚጠቅም የትርጓሜ ሂደት ነው[1] ። በአንድምታ መጻህፍቶች ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት ከሁሉ በላይ ትርጓሜ ያገኘው የዮሐንስ ራዕይ 6፡2 ሲሆን በዚህ ምንባብ የሚገኘው ነጭ ፈረስ 19 አንድምታወች ይዞ ይገኛል::[2]

«አንድ ትርጓሜ እንዲህ ነው፤ አንድም እንዲህ፤ አንድም...» ከማለት እያንዳንዱ ትርጓሜ «አንድምታ» የተባለው ነው፣ «አንድምታ» ለመላው ትምህርት ዘርፍ ለመሰይም ችሏል።

የአንድምታ መጻህፍት የመጽሃፍ ቅዱሳትን እንግዳ ቦታወችና አስተሳሰቦች ከ18ኛው ክፍለዘመን ኢትዮጵያ ቦታወችና አስተሳሰቦች አንጻር በማገናዘብ ያስረዳሉ። ለአንድምታ መነሳትና መስፋፋት ከፍተኛ ሚና የነበረው የፖርቱጋል ካቶሊኮች በአጼ ፋሲለደስ መባረር ነበር። ከዚህ በኋላ በተካሄደው ስራ መምህር ኢሶዶሮስ እና ከሱ በኋላ የተነሳው አቃቤ ሰዓት ሃብቴ በሰፊው ለዚህ ስራ በማበርከት ይጠቀሳሉ። ስለዚህ ሰፊ ጥረታቸው የአንድምታ ትምህርት ከቅኔና ከንባብ ቤት ትምህርት ማለፍ ቀጥሎ የሚሰጥ ልዩ ትምህርት ሆነ።

[እንዲሁም]

"አንድምታ" (Andemta) በቅርቡ የተጀመረች የጥበብ መጽሔት ስም።[3]

  1. ^ "የወንጌል አንድምታ debelo.org ላይ ይመልከቱ". Archived from the original on 2019-01-08. በ2019-02-03 የተወሰደ.
  2. ^ Abraha, Tedros & Kirsten Stoffregen, Encyclopaedia Aethiopica, (edited by Siegbert Uhlig), Harrasowiz Verlag, 2003
  3. ^ www.andemta.com