ኣጠፋሪስ

ከውክፔዲያ
Datura stramonium

ኣጠፋሪስ ወይም አስተናግርት (Datura stramonium) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

(ስሙ ኣጠፋሪስ ከ«እጸ ፋርስ» ጋር የተዛመደ ይሆናል፣ አሁን ግን «እጸ ፋርስ» በተለመደ ለCannabis sativa ያጠቆማል።)

(ሌላም ዝርያ Nicandra physalodes ደግሞ «አጠፋሪስ» ተብሏል።)

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አስተዳደግ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በእርሻዎች ውስጥ በመስክም በጣም ተራ ክረምታዊ አረም ነው።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የተክሉ ጥቅም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዘሮቹም ቅጠሎቹም እንደ መድኃኒት ይጠቀማሉ።

የተደረቁ የተደቀቁ ቅጠሎች ከቅቤ ጋራ ተቀላቅለው እንደ ፀረ-ሻገቶ ለፎረፎር/የአናት ልክፈት፣ ወይም አንዳንዴም በመልክ ላይ ይጠቀማሉ። ቅጠሎቹ ተደቅቀው ለጥፍ ተደርገው የጭነት ከብት ቁስል፣ ወይም የሰው ቁስል ወይም ጭርት ያክማል።

የተፈሉ ዘሮች ፍልፋይ ወይም ቅጠሎች እንፋሎት የጥርስ ሕመም ለማስታገስ ይናፈሳል።[1]

ጥቁር ዘሮቹ በጣም ገዳይ መርዛም ናቸው። በጣም ጥቃቅን መጠን ማሳበድ ይችላል። ተክሉ በሙሉ መርዛም ይቆጠራል፣ አይበላም።[2]

  1. ^ የዘጌ ልሳነ ምድር ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 1999 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
  2. ^ አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.