ካሊጎላ

ከውክፔዲያ
ካሊጎላ

ካሊጉላ (ሮማይስጥ፦ Gaius Julius Caesar Augustus Germanicus) (ከ8 ዓ.ም. እስከ 33 ዓ.ም. የኖረ) ከ29 ዓ.ም. እስከ 33 ዓ.ም. የነገሠ የሮሜ መንግሥት ቄሣር ነበረ።

«እኔ አምላክ ነኝ» የሚል ጨካኝ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ይታወሳል። አይሁዶች እንዲያመልኩት እምቢ በማለታቸው የእርሱ ሐውልት በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ እንዲቆም አዘዘ። በዚያው ሥራ ዓመጽ እንዲስፋፋ እርግጥኛ ይሆን ነበርና የሶርያ አገረ ገዥ ፑብሊዩስ ፔትሮኒዩስ ለአንድ ዓመት ዘገየ። በመጨረሻ ካሊጎላ በወዳጁ ሄሮድያስ አግሪፓ ምክር ሀሣቡን መለሠ። በተረፈ ግን በአይሁዶች ዘንድ በዚህ ዘመን ብዙ ሁከቶች ሆኑ። ካሊጎላም ዕብድ ነው በማለት የታሪክ ጸሐፊዎች ይስማማሉ። ፈረሱን ኢንኪታቱስን ቄሥ ሹሞት ለሮሜ ሴናት አማካሪ እንዲሆን ወሰነ። በ33 ዓም ካሊጉላ በግድያ ሞተ።