ኮባ

ከውክፔዲያ
የእንሰት ዝግጅት፣ 1882 ዓ.ም.

ኮባ (ጉናጉና ወይም እንሰት) ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ለምግብነት የሚጠቅም የተክል አይነት ሲሆን ለምግብ የሚያገለግለው ስር እንሰት በመባል ይታወቃል። ብዙ የኮባ አይነቶች በአፍሪካ ደጋማ ክፍሎች ይብቀሉ እንጂ በለማዳ እጽዋትነት እየበቀለ ለምግብነት የሚያገለግለው በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። የኮባ ተክል በጥንቱ የግብጽ ስልጣኔ ይበቅል እንደነበር ማስረጃ አለ።

የኮባ ቅጠል ዳቦ ለመጋገርና ቃጫ ለመስራት ሲያገለግል እንሰት የተሰኘው ስሩ ደግሞ ለቆጮ፣ ለቡላና መሰል ምግቦች መስሪያነት ያገለግላል። ኮባ ከሌሎች ተክሎች በተለየ መልኩ ዳገታማ ቦታ ላይ ስለሚበቅል ለተራራማ ቦታወች የተመቻቸ ተክል ነው። ሌላው ጥሩ ጸባዩ ድርቅን መቋቋሙ ነው። አንድ የኮባ ተክል ከተተከለ በኋላ ከ4-5 ዓመት ውስጥ ለምግብነት ይደርሳል። እያንዳንዱ የኮባ ስር (እንሰት) እስከ 40 ኪሎግራም ዱቄት ይወጣዋል።

የኮባ ተክል በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢ ይኑር እንጂ በአሁኑ ወቅት ለምግብነት የሚያገለግለው በደቡባዊ ምዕራብ የአገሪቱ ክፍል ነው። ተመራማሪወች የዚህ ምክንያቱ በጥንቱ ዘመን የኮባ ተክል ለምግብነት በሁሉ የኢትዮጵያ ክፍል ዘመን ያገለግል ነበር ሆኖም ግን እርሻና የዓዝርዕት ተክል እየተሰፋፋ ሲሄድ የኮባ ምግብነት እየተረሳ ሄደ። [1]

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2008-05-17. በ2010-11-28 የተወሰደ.