ዲምቱ

ከውክፔዲያ
ዲምቱ
ከተማ
አገር  ኢትዮጵያ
ክልል ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
ዞን ወላይታ
ወረዳ ድጉና ፋንጎ
ካንቲባ ኢዩኤል ሞላ
ከፍታ 1,400 ሜ.
ዲምቱ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ዲምቱ
የዲምቱ ፡ አቀማመጥ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ውስጥ

6°55′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°07′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


ዲምቱ ወይም ወላይታ ዲምቱ ከተማ በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን የሚትገኝ ከተማ አስተዳደር ናት። ከተማዋ ከዚህ ቀደም በነበረው አወቃቀር በዳሞት ወይዴ ወረዳ ስር የነበረች ቢሆንም፣ አሁን ግን በድጉና ፋንጎ ወረዳ ስር ትገኛለች።[1]

ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዴቪድ ቡክሰን የተባለ ጻሓፊ፥ ዲምቱ በብላቴ ወንዝ አካባቢ የሚገኝ የገበያ ስም እንደሆነ ጽፎ ነበር።[2] አንዳንድ አፈታሪኮች እንደምጠቁሙት ከሆነ ገበያው ስያሜውን ያገኘው ከከተማዋ የሚወጣ ትንሽ ንጹህ ወንዝ ከብላቴ ወንዝ ጋር በሚገናኙበት ገበያው ይቆም ስለነበረ ነው። ይህን መገናኘት በወላይትኛ ዳንቷ እያሉ ይጠሩትም ነበር፤ መገናኛ ማለት ነውና። ከጊዜና ከቃሉ አጠራር ዘዬ ጋር ተያይዞ የአሁኑን ስያሜ ይዞ ለከተማውም ስም ሆኖ አረፈው ይባላል። ዲምቱ በወላይታ ውስጥ ከሶዶ ቀጥሎ እጅግ ረጅም ዕድሜ ያስቆጠረች ከተማ ናት። ከተማዋ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምዕራብ 333 ኪሎ ሜትር ርቃ የሚትገኝ ሲሆን፥ ከዞኑ ዋና ከተማ ሶዶ ደግሞ በ68 ኪሎ ሜትር ርቀት በስተምሥራቅ ትገኛለች። ከተማዋ በስተምሥራቅ በብላቴ ወንዝ የሚትዋሰን ሲሆን ውንዙ ከሲዳማ ክልል እና ከኦሮሚያ ክልል በተመሳሳይ ሁኔታ ያገናኛታል።

ዋቢ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "Admirative Map of SNNPR". በ6 October 2020 የተወሰደ.
  2. ^ David, Buxton. David Roden Buxton. David Roden Buxton. pp. 66.