ዶን ወንዝ

ከውክፔዲያ
ዶን ወንዝ (ጤና)
የዶን ተፈሳሽ
የዶን ተፈሳሽ
መነሻ ሩሲያ
መድረሻ የአዞቭ ባሕር
ተፋሰስ ሀገራት ሩስያዩክሬን
ርዝመት 1,950 km (1,212 mi)
አማካይ ፍሳሽ መጠን 935 m³/s
የተፋሰስ አካባቢ ስፋት 425,600 km² (164,324 mi²)


የዶን ወንዝ (ሩስኛДон) በሩሲያ የሚገኝ ዋና ወንዝ ነው። መነሻው ኖቮሞስኮቭስክ በሚባለው ከተማ ሲሆን እስከ አዞቭ ባሕር ድረስ የፈስሳል።

በጥንታዊ ዘመን አገሩ እስኩቴስ በተባለው ጊዜ ግሪኮች ወንዙን «ጣናይስ» አሉት። የግሪክ ነጋዴዎች ጣናይስ የተባለ ቅኝ ከተማም በአፉ መሠረቱ።

1722 ዓ.ም. አስቀድሞ ይህ ወንዝ የአውሮፓና የእስያ ጥንታዊ ጠረፍ ሆኖ ይቆጠር ነበር። በዚያን አመት የአውሮፓ ጠረፍ እስከ ኡራል ወንዝ እንዲዘረጋ የሚል ሀሣብ ለመጀመርያ ጊዜ ቀረበ።[1]

መጽሐፈ ኩፋሌ መሠረት (9፡2፣ 6፣ 13) ከምሥራቁ ጫፍ («ራፋ») ጀምሮ በአዞቭ («ሜአት» ወይም «ሜኦት») ባሕር ወዳለው እስከ አፉ ድረስ፣ ይህ ወንዝ («ጤና ወንዝ» ተብሎ) ከኖኅ ልጆችሴምና ከያፌት ርስቶች መካከል የሆነው ጠረፍ ይሠራል። ጠረፉም ከዚያ ከምሥራቁ ጫፍ ቀጥታ ወደ ምሥራቅ ይሄዳል። በኩፋሌ 9፡21 ደግሞ፣ ከምሥራቁ ነጥብ እስከ መነሻው ድረስ ከዚያም ቀጥታ ወደ ስሜን የሆነ መስመር ከያፌት ልጆች ከጋሜርና ከማጎግ ርስቶች መካከል የሆነው ጠረፍ ነበር። ይህ በተለይ በአራማይስጥ ትርጉም ይታያል።

ሀንጋሪ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ ወንድማማች ሁኖርና ማጎር በዚህ ሸለቆ አዳኞች ሆነው ኖሩ።

ነጥቦች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]