Jump to content

ራዲዮ ስቱዲዮ 54 ኔትወርክ

ከውክፔዲያ
የራዲዮ ስቱዲዮ 54 ኔትወርክ ምልክት

ራዲዮ ስቱዲዮ 54 ኔትወርክ የግል ራዲዮ ጣቢያ በሎክሪካላብሪያጣልያን አገር ነው። የጣቢያው ማሠራጨት ዙሪያ እስከ ፱ ደቡባዊ ክፍላገሮች ድረስ ይደርሳል፤ እነርሱም መሢናረጆ ካላብሪያቪቦ ቫሌንቲያካታንዛሮኮሰንዛክሮቶኔለቼፖተንዛ፣ እና ሳሌርኖ ናቸው። በጣቢያው ላይ ዘመናዊ ሙዚቃ ዘፈኖችና በየቀኑ 28 ጊዜ የዜና መረጃ ይሠጣል።

ስቱዲዮ 54 ኔትዎርክ የተመሠረተው በ6 June 1985 እ.ኤ.አ. በመሥራቾች ፔትሮ ፓሬታ፣ ፍራንቼስኮ ማሣራ፣ ኤንዞ ጋቶ፣ መሞ ሚኒቲ፣ እና ፔትሮ ሙስሜቺ ሲሆን ስሙ «ራዲዮ ዲጄ ክለብ ስቱዲዮ 54» ተብሎ ነበር። እንደ ሌሎቹ ነፃ ጣልያናዊ ራዲዮ ጣቢያዎች፣ ይህ እንደ ጨዋታ ትርዒት ጀመረ። በ1990 እ.ኤ.አ. በጣልያናዊ ሕግ ሥር ይህም የጨዋታ ትርዒት በይፋ ድርጅት ሆነ፣ በዚህም የጣቢያው ፕሮፌሽናሉ መልክ ተጨመረ።

1991 እ.ኤ.አ. ደግሞ ከሁሉ ካላብሪያ መጀመርያው ራዲዮ ዳታ ሲስተም የሚባል ሲስተም የሚጠቅመው ራዲዮ ጣቢያ ሆነች። ይህም ከጣልያን ሁሉ ከፊተኞቹ መካከል ነው። በ1994 እ.ኤ.አ. ማሠራጨቱ በኮምፒውተር በዲጂታል አማካኝነት እንዲሆን በቃ፤ ከበፊቱም ማሠራጨቱ ጥረትና ፍትነት አገኘ። ከ1995 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ሌሎች የካላብሪያ ራዲዮ ጣቢያዎች በክፍያ በመግዛቱ፣ ማሰራጨቱ የሚደርስበት ርቀት ተጨመረ። በ1997 እ.ኤ.አ. እንደገና ከጣልያን ፊተኞች መካከል ሲሆን፣ የዌብካስቲንግ ችሎታ በሪል ኦዲዮ ሶፍትዌር ጀመረ።

1998 እ.ኤ.አ. ስሙ «ስቱዲዮ 54 ኔትወርክ» ሆነ፤ በተጨማሪ ከ2000 እ.ኤ.አ. ጀምሮ «ስታርጌት» የተባለው ተዛዋሪ ስቱዲዮ በመሥራቱ፣ ማሠራጨት ከአደባባይ ሕዝብ በቀጥታ ተቻለ።

Rossella Laface, Alex Albano, Enzo DiChiera, Paolo Sia, Demetrio Malgeri, Marika Torcivia, Franco Siciliano, Mara Rechichi, Luigi Di Dieco