ታማኝ በየነ
የዚህ መጣጥፍ የማያደላ ዝንባሌ ያለው ሁናቴ መኖሩ አጠያያቂ ጉዳይ ነው። (መግለጫውን በውይይት ገጽ ላይ ይፈልጉ።) |
ጊዜው ገና ኢህአዴግ እንደገባ ነው የወያኔ ታንኮች ገና አልቀዘቀዙም ታጋዮቹም የገደሏቸው ሰዎችን ደም ከእጃቸው ላይ አላፀዱም በደም እንደተጨማለቁ ነበሩ የኢህአዴግን ስርዐት መቃወም ቀርቶ ኢህአዴግ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ህዝቡ በግልፅ ባላወቀበት ዘመን አንድ ጀግና ወጣት አዲስ አበባ ስታድየም መድረክ ላይ ማይኩን ጨብጦ ወጣ እንዲህም አለ
የወንድ ቅድመ አያቴ ከመንዝ ተነስቶ
በቾ ተቀመጠ አንድ ኦሮሞ አግብቶ
ያቺ ኦሮሞይቱ የኔ ሴት ቅድመአያት
ልጅ ወልዳ አሳደገች የኔን እናት አባት
ለአቅመ ሔዋንም ስትደርስ በጥሩ እንዳደገች
ከመቀሌ የመጣ አንድ ትግሬ አገባች
ይህ የአያቶቼ ልጅ ይህ የተወለደው
አባቱ ነው ትግሬ አማራ ኦሮሞ ነው
ለአቅመ አዳምም ሲደርስ አንዲት ውብ ልጅ ወዶ
ልትኖር አዲስ አበባ የመጣች ከሶዶ
ጉልቻ ጎልተው ሲኖሩ ተዋደው
አብረው ፍሬም አዩ እኔን ወንዱን ወልደው
ኦሮሞም ትግሬም ነኝ ጉራጌም አማራ
ዘሬ ማን ሊባል ነው ማን ተብዬ ልጠራ
ዘሬም ዜግነቴም በአንድነት አንድ ነው
ዘሬን አትጠይቂኝ ዘሬ ኢትዮጵያዊ ነው
~ታማኝ በየነ @አዲስ አበባ ስቴድየም
በመጨረሻም ለህዝቡ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቀረበ
"ትወዱኛላቹህ?"
ከክብር ትሪቡን በስተቀር ሚስማር ተራ፣ ካታንጋ፣ ዳፍትራክ፣ከማን አንሼ እና ጥላ ፎቅ የነበረ የያኔው የኢትዮጵያ ልጅ በአንድ ቃል እንዲህ አሉት
"ታማኝ እንወድሀለን፡፡"[1]
ታማኝ በየነ ከእናቱ ከወ/ሮ ማሚቴ ቢተው እና ከአባቱ ከግራ አዝማች በየነ ወንድይፍራው በሰሜን ኢትዮጵያ ጭልጋ የተባለ ጎንደር ውስጥ በሚገኝ ስፍራ ተወለደ ጀግናው ቀጠለ "አሜን መወደድ አያሳጣኝ"