Jump to content

ኔልስ ቦር

ከውክፔዲያ
ኔልስ ቦር በ1914 ዓም

ኔልስ ቦር (ዳንኛ፦ Niels Bohr) 1878-1955 ዓም የዴንማርክ ፊዚሲስት ነበር። የቁስ አካላት መሰረታዊ ክፋዮች የሆኑት አቶሞች እንግዳ ግኝት በነበሩበት በ፳ኛው ክፍለ ዘመን አጥቢያ፤ ስለ እነርሳቸው ተፈጥሮና ባህርይ መሰረታዊ ምርምር በማቅረብ አዲሱን የሳይንስ ዘመን ከከፈቱት ሳይንቲስቶች አንዱ ነበር። በተጨማሪ ፣ የኳንተም ኃልዮትን መሰረት ከጣሉት ሳይንቲስቶች አንዱ ሲሆን፣ ስለዚህ መትጋቱ የኖቤል ሽልማት አግኝቷል።