Jump to content

አዳዲስ ቀልድ

ከውክፔዲያ
በቅርቡ አንድ ሰዉ ይታሰራሉ ከዚያም አንዱ ለጓደኛዉ “አንተ እገሌ እኮ ታሰረ” ይለዋል። 
“እንዴ ምን አድርጎ አሰሩት” ይለዋል
“ሰርቆ ነዋ”
“ሰርቆ አይ ልክስክስ በደንብ አልሰረቀም ማለት ነዉ”
“ምን ማለትህ ነዉ ይህን ስትል አልገባኝም”
“ይህ እንዴት አይገባህም በደንብ ቢሰርቅማ ፓርላማ ይገባ ነበራ”
የወያኔ ሴኮሪቲ
-“በስብሰባችሁ ላይ የእኛ ሁለት ሰዎች ይገኛሉ”
-“ሁለት ብቻ?”
-“አዎን ሁለት ይበቃሉ የምትናገረዉን ይመዘግባሉ”
-“ለመጽሐፍ እንዳይቸገሩ ቀስብዬ እናገራለሁ”
አንድ ዳኛ
አንድ ዳኛ ለቀረበላቸዉ ክስ ምስክሮችን አዳምጠዉ የቀረቡትን መረጃወች አመሳክረዉ በሕጉመሰረት ፍርዳቸዉን ከሰጡ በሁዋላ። ወደ ቢሯቸዉ ገብተዉ በሳቅ ይንፈቀፈቃሉ። 
ከዚያም ባልተለመደዉ ሁኔታቸዉ በጉዳዩ የተደነቀዉ ጓደኛቸዉ ምን እንደዚህ የሚያስቅ ነገር አጋጠመህ ይላቸዋል። 
ዳኛዉም እንደምንም ሳቃቸዉን እየተቆጣጠሩ ዛሬ ያጋጠመኝ ክስና ሃያ ዓመት የፈረድሁበት ተከሳሽ ተናገረ ተብሎ የተከሰሰበት ተገቢ ያልሆነ ቀልድ እንዴት አይነት 
የሚያስቅ ቀልድ መሰለህ ቀልዱን ይነግረኛል ብለህ ግን አትጠብቅ አንተ መቼም መንገርም እንደሚያስቀጣ ሕጉን በደንብ ታዉቃለህ አሉት።
	ሁለት እስረኞች በቃሊቲ
-አንተን ስንት ፈረዱብህ
-ሃያ ዓመት ፈረዱብኝ
-የእኔም ሃያ ዓመት ነዉ። ለምንድን ነዉ ሃያ ዓመት የፈረዱብህ።
-ምንም አላደረግሁም ዝም ብለዉ ነዉ።
-አትዋሽ ምንም ላላደረገማ አስር ዓመት ነዉ የሚፈርዱት።
	የሐብታሙ ሰዉ ዘመድ
አንድ በዉጭ አገር የሚኖር ትዉልደ ኢትዮጵያዊ ሚሊዮነር አይናቸዉን ይታወራሉ። በአገር ቤት ለሚኖረዉ ዘመዳቸዉ ወደ ሚኖሩበት አገር ሄዶ እንዲረዳቸዉ ጥሪ ያደርጉለታል። 
እሱም ለመሄድ ፕሮስስ ይጀምራል የወያኔ ባለስልጣናት ለምንና ወዴት ለመሄድና እንደሚዘጋጅ ይደርሱበትና አስጠርተዉ ይጠይቁታል። እሱም ሁኔታዉን ያስረዳቸዋል። 
ከዚያም ለምን ዘመድህ ከዚያ ያላቸዉን ድርጅታቸዉን ሽጠዉ ገንዘባቸዉን ወደዚህ አዛዉረዉ ከዚህ አገራቸዉ ገብተዉ በሰላም አይኖሩም። እኛም በመንግስት በኩል የሚያስፈልገዉን ሁሉ 
ከዚህ እናዘጋጅላቸዋለን። ለምን ይህን ለዘመድህ አትጽፍላቸዉም አታስረዳቸዉም ይሉታል። ሰዉየዉም ወንድሞቼ የተናገርሁት የገባችሁ አይመስለኝም።
 ዘመዴ እኮ አይኑን ታወረ እንጅ መቼ አበደ አልሁኝ አሏቸዉ ይባላል
	አንድ የኢሕአድግ ታጋይ
አንድ የኢሕአድግ ታጋይ ሥራዬንም አካባቢዬንም እለቃላሁ በማለት ማመልከቻ ለአለቃዉ ያቀርባል። አለቃዉም ያስጠሩትና ምነዉ አንተ በጣም ጥሩ ታጋያችን ነህ፣ 
ታማኛችንም ነህ ደመወዝም እንጨምርልሃለን፣ እድገትም እናደርግልሃለን ለምን ነዉ ሥራ ለቀህ የምትሄደዉ ይሉታል። 
“ጌታዬ ጎረቤቶቸና የሚቀርቡኝ ሰወች ሁሉ የወያኔ ስራት ማለቂያዉ ተቃርቧል አሁን ብትለቅ ይሻልሃል ያለዚያ ዋጋህን ታገኛለህ እያሉ ይዝቱብኛል ስለዚህ ለቅቄላቸዉ እሄዳለሁ።”  
አለቃዉም ሊአረጋጉት “የወያኔ ሥራት መቼም ማለቂያ የለዉም አትፍራ” ይሉታል 
“እሱም እንግዲያዉስ ሌላዉ ምክንያት ነዉ ጌታዬ!” አላቸዉ
{ምንጭ እኔ እራሴ አበጄ}