የተፈጥሮ ቁጥር (ናቹራል ነምበር)

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

‎ በሂሳባዊ አጠቃቀም የተፈጥሮ ቁጥር የሚባሉት ነገሮችን ለመቁጠር (8 ተማሪዎች አሉ።) እና ደረጃን ለመግለጽ ( ወደ አዲስ አበባ ስመጣ 4ኛ ግዜዬ ነው።) የመንጠቀመባቸው ቁጥሮች ናቸው።

አልጀብራዊ ባህሪዎች [ለማስተካከል]

ድምር (+) እና ብዜት (×) በመጠቀም በተፈጥሮ ቁጥሮች ላይ የተወሰኑ ጸባዮችን ማየት ይቻላል።

  • በድምር እና ብዜት ዝግ፡ ለማንኛውም ሁለት የተፈጥሮ ቁጥሮች መ እና ቀ ካሉን፣ መ+ቀ እና መ×ቀ ሌላ የተፈጥሮ ቁጥር ይሰጣሉ
  • የልዩ አባል መኖር፡ ለማንኛውም የተፈጥሮ ቁጥር መ፣ መ+0=መ እና መ×1=መ
  • በዜሮ አለመካፈል፡ ለማንኛውም ሁለት የተፈጥሮ ቁጥሮች መ እና ቀ ካሉን፣ መ×ቀ=0 ከሆነ መ=0 ወይም ቀ=0