መለጠፊያ:ምርጥ ፅሑፎች

ከውክፔዲያ

ምርጥ ፅሑፎች (ዕጩዎች ይምረጡ!)


ቢግ ማክሃምበርገር ዓይነት ሲሆን በፈጣን ምግብ ቤቱ ማክዶናልድስ የሚሸጥ ነው። ሃምበርገሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው በ1960 ዓ.ም. በአሜሪካኑ ጅም ዴልጋቲ ነበር። ሁለት የተፈጨ የበሬ ስጋ ክቦችን፣ ሰላጣ ቅጠል፣ ዓይብ፣ ሽንኩርት፣ ፒክልስ እና ሶስት የሰሊጥ ጠፍጣፋ ዳቦዎችን ከማዋዣ የቢግ ማክ ሶስ (መረቅ) ጋር ይይዛል።

ቢግ ማክ በኣሁኑ ዘመን በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተዎዳጅነትን በማግኘቱ ዘ ኢኮኖሚስት የተሰኘው የሥነ ንዋይ ጋዜጣ በያመቱ ቢግ ማክ ኤንዴክስ የተባለ መረጃ ያትማል። ቢግ ማክ በያገሩ የሚሸጥበትን ዋጋ በማዎዳደር፣ የየአገሩን የኑሮ ውድነት ለማነጻጻር ይጠቀምበታል።


ታሪክ በዛሬው ዕለት (ጁን 1, 2024 እ.ኤ.አ.)

ግንቦት ፳፬

  • ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በ፳ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በትልቅነቱ በኢትዮጵያ ታሪክ አቻ የሌለው በ”ሪክተር” ሚዛን ስድስት ነጥብ ሰባት ያስመዘገበ የመሬት እንቅጥቅጥ ተከስቶ የማጀቴን ከተማ ሲደመስስ፣ በጎረቤቷ ካራቆሬ ደግሞ ከመቶ እጅ አርባ አምሥቱ መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። ከካራቆሬ በስተሰሜን የሚያልፈው ዋናው የአዲስ አበባአስመራ መንገድ እና ድልድዮችም እንቅጥቅጡ ባስከተለው የድንጋይ ናዳ ወደ አሥራ ሰባት ኪሎ ሜትር ርዝመት ላይ አደጋ ደረሰ።
  • ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - ከዘጠኝ ወራት በኋላ ነጻነቷን የተቀዳጀችው ኬንያ፣ በዛሬው ዕለት እራሷን የማስተዳደር መብት ተፈቀደላት። ይሄንን ዕለት በየዓመቱ “የማንዳራካ ቀን” በሚል ስያሜ ኬንያ ታከብረዋለች።
  • ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - በቀድሞዋ ሮዴዚያ (አሁን ዚምባብዌ) በ፺ ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቁሮች የሚመራ መንግሥት ሥልጣንን ጨበጠ።
  • ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - ‘ሲ. ኤን. ኤን.’ (CNN) የተባለው የዜና ማሠራጫ ድርጅት ሥራውን ጀመረ።
  • ፲፱፻፺፫ ዓ/ም - የኔፓል አልጋ ወራሽ ልዑል ዲፔንድራ አባታቸውን ንጉሥ ቢሬንድራን፤ እናታቸውን ንግሥት አይስዋርያን እና ሌሎችንም ንጉሣዊ ቤተ ሰባቸውን ረሽነው ከገደሉ በኋላ እራሳቸውንም በጥይት አጠፉ።