Jump to content

ኢየሩሳሌም ሰማያዊት

ከውክፔዲያ

ኢየሩሳሌም ሰማያዊት የሰማይ መካከል ናት ከላይ ሶስት ከታች ሶስት ሰማያት ይገኛሉ በዚህች ሰማይ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በስተቀር ምንም አይነት ፍጥረት አይኖርም ይህች ሰማይ ሳጥናኤል የተፈጠረባት ከዚያም የወጣባት ናት ይህች ሰማይ በሳጥናኤል ምትክ ለተፈጠረው የሰው ልጅ ተሰጥታ ቢሆንም ነገር ግን በሰይጣን ዲያብሎስ አሳችነት ሊኖርባት አልቻለም አዳም ዕጸ በለስን ሳይበላ 1000 ዓመት ቢኖር ታድሶ መንግስተ ሰማያትን ይወርስ ነበር ሳጥናኤል ወደ ምድር ሲወድቅ እግዚአብሔር ሰማይን ይዞ ሸሸ ብሎ ተናገረ ነገር ግን ኢየሩሳሌም ሰማያዊት እንደጸናች ናት ይሁን እንጂ በኋላኛው ዘመን በትንሳዔ ዘጉባኤ ጻድቃን የሚወርሷት የክርስትያኖች ርስት ናት ኢየሩሳሌም ሰማያዊት 12 ደጆች አሏት የብርሃን መጋረጃ ከላይ ወደታች የተጋረደባት ናት በመሰረቷ ላይ የ12ቱ ሐዋርያት ስም ተጽፎባታል መንግስተ ሰማያት ወደ የት ነው የምትገኘው ቢሉ ከሰማይ ውዱድ በታች ከኢዮር በላይ ናት