ማኒላ

ከውክፔዲያ

ማኒላ (እንግሊዝኛ፦ Manila) የፊሊፒንስ ዋና ከተማ ነው።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 10,677,000 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 1,581,082 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 14°37′ ሰሜን ኬክሮስ እና 120°58′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

የከተማው ስም የተነሣ ከታጋሎግ ስሙ 'ማይኒላድ' (የኒላድ አበባ ሥፍራ) ነው። በ1562 ዓ.ም. ስፓንያውያን ወርረውት በ1587 የፊሊፒንስ ዋና ከተማ ሆነ።