ማንችስተር ዩናይትድ
| ሙሉ ስም | ማንችስተር ዩናይትድ የእግር ኳስ ክለብ | |||
| ቅጽል ስም(ሞች) | ቀያይ ሰይጣኖች | |||
| ምሥረታ | 1878 እ.ኤ.አ. | |||
| ስታዲየም | ኦልድ ትራፎርድ | |||
| ባለቤት ሊቀመንበሮች ዋና አሰልጣኝ (አስተዳዳሪ) |
ማልኮም ግሌዘር ጆል ግሌዘር እና አቭራም ግሌዘር ሰር አሌክስ ፈርጉሰን |
|||
| ሊግ | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ | |||
| ድረ ገጽ | ይፋ ድረ ገጽ (እንግሊዝኛ) | |||
|
|
||||
ማንችስተር ዩናይትድ የእግር ኳስ ቡድን ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ዋና ተካፋይ ነው። የሚጫወተው በራሱ ሜዳ ኦልድ ትራፎርድ ውስጥ ነው። ክለቡ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 18 የሊግ ዋንጫዎችን በማንሳት ሪከርድ ያለው ሲሆን 11 ግዜ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ በማንሳትም ታሪክ ያለው ክለብ ነው። በሀብት እና በደጋፊ ብዛት ታላላቅ ከሆኑት የአለማችን ውጤታማ ክለቦች አንዱ ነው። ይህ ቡድን በቅጽል ስሙ ቀያይ ሰይጣኖች ወይም በእንግሊዝኛው The Red Devils በመባል ይታወቃል። ክለቡ የተመሰረተው ቤ.አ.አ. 1878 Newton Heath LYR F.C. በሚባለው የመጀመሪያ መጠሪያው ነበር። ከዚያም የሀገሪቱን ሊግ የተቀላቀለው እ.አ.አ. በ1892 ነበር. ከ1938 እ.አ.አ. ጀምሮ የሀገሪቱ ዋና የእግር ኳስ ክፍል መጫወት (ከእ.አ.አ. 1974-75 አመት በስተቀር) ጀመረ። የአውሮፓን ዋንጫ በእ.አ.አ. 1968 በማሸነፍ እና የሶስትዮሽ ዋንጫን እ.አ.አ. በ1999 በማሳካት የመጀመሪያው የእንግሊዝ ክለብ ነው። እ.አ.አ. በኖቬምበር 6፣ 1986 የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ይባላሉ።
የመጀመሪያው ቡድን አባላት ዝርዝር [ለማስተካከል]
1. ኢድዊን ቫን ደር ሳር
3. ፓትሪስ ኢቭራ
4. ኦውን ሃርግሪቭስ
5. ሪዮ ፈርዲናንድ
6. ዌስ ብራውን
7. ማይክል ኦውን
8. አንደርሰን
9. ዲሚታር ቤርባቶቭ
10. ዌይን ሩኒ
11. ራየን ጊግስ
12. ክሪስ ስሞሊንግ
13. ፓርክ ጂ-ሱንግ
14. ሃቪየር ኸርናንዴዝ
15. ኒማኒያ ቪዲች
16. ማይክል ካሪክ
17. ናኒ
18. ፖል ስኮልስ
20. ፋቢዮ
