ምላስ

ከውክፔዲያ
ምላስ

ምላስአፍ ወለል ላይ የሚገኝ ጡንቻማ አካል ሲሆን ምግብን በሚገባ ለማላመጥ እና ለመዋጥ ይረዳል። የላይኛው የምላስ ክፍል በጣዕም ህዋሳት የተሸፈነ በመሆኑ ጣዕምን ለመለያ ዋና አካል ነው። ሁለተኛው የምላስ (ልሳን) ጥቅም ለንግግር ነው። ምላስ እጅግ በጣም ስሜታዊ አካል ሲሆን በሳሊቫ (saliva - ምራቅ) የተሸፈነ ነው። ብዛት ያላቸው የደም ቧንቧዎች እና የነርቭ ጫፎች ይይዛል። እነዚህም በተፈለገበት አቅጣጫ እንዲንቀሳቀስ ይረዱታል።