ሳይሌሲያን
ከውክፔዲያ
የሳይሌሲያን ቋንቋ (ሳይሌሲያን፦ ślůnsko godka, ślůnski, አንዳንዴ ደግሞ pů našymu) በፖላንድ የላይኛው ሳይሌሲያ ክፍለ ሀገር፣ በቼክ ሪፑብሊክ እና በጀርመን ሀገር የሚነገር ቋንቋ ነው። በ2002 እ.ኤ.አ. በፖላንድ በተካሄደው ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራ 56 ሺ ሰዎች ሳይሌሲያን የመጀመሪያ ቋንቋቸው እንደሆነ አስመዝግበዋል። አንዳንድ የቋንቋ ሊቃውንት የሳይሌሲያን ቋንቋ ከፖልኛ ቋንቋ ጋር በቅርብ የተዛመደ በመሆኑ፣ እንደ ቀበሌኛ አነጋገር ይቆጥሩታል
የሳይሌሲያ ቋንቋ ተናጋሪዎች የራሳቸው ፊደላት ስላልነበራቸው ለጽሑፍ የፖልኛን ፊደላት ይጠቀሙ ነበር። በ1998 በ10 የሳይሌሲያን ፊደላት እና ዲግራፎች (digraphs) የተመሠረተ የአጻጻፍ ደንብ ተፈጥሮ፣ በኢንተርኔትና በሳይሌሲያን ዊኪፔድያ የተስፋፋ ጥቅም ላይ ውሏል።
[ለማስተካከል] ማስታወሻ
- http://www.nowiny.pyrsk.com/ (ዜና በሳይሌሲያን)
| ጅምር! (ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ!) |