ስኳር በሽታ

ከውክፔዲያ
ዓለም አቀፉ ሠማያዊ ክብ የስኳር በሽታ ውክል ነው።

የስኳር በሽታ (diabetes mellitus) አንድ ሰው አለው ስንል በደሙ ውስጥ ያለው የስኳር መጠን (serum glucose level) መሆን ከሚገባው በላይ ከፍ ብሏል ማለት ነው። ይሕ በሽታ አብዛኛውን ጊዜ በሂደት እና ከብዙ አመታት በኋላ የሚከሰት ነው። በመሆኑም እድሜያቸው ከ40 በላይ የሆኑ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ሲጠቁ ይታያል ። አንድ ጥናታዊ ፅሑፍ እንደሚያመለክተው በጎንደር ከተማ እድሜያቸው ከ40 አመት በላይ ከሆኑት ሰዎች መካከል 2.4% የሚሆኑት የዚህ በሽታ ተጠቂ ናቸው ። ይህ አሃዝ አሳሳቢ መስሎ ላይታይ ይችላል። ነገር ግን በሽታው በተለይ ወፍራም (over weight) እና/ወይም አዘውትረው የአካል እንቅስቃሴ የማያደርጉ ሰዎችን የሚያጠቃ ስለሆነ፤ በተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ግለሰቦች በሚበዙበት ትልልቅ ከተሞች በርካታ ሐበሻ የስኳር በሽታኞች እንዳሉ እሙን ነው።

የስኳር በሽታ ሁለት ዓይነቶች ናቸው።

ደግሞ ይዩ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ለስኳር በሽታ በባህላዊ ሕክምና ይዩ፦