ቀቿ

ከውክፔዲያ
ቀችዋ የሚገኝባቸው ክልሎች

ቀቿ (Qhichwa Simi / Runa Shimi / Runa Simi) በደቡብ አሜሪካ በ10 ሚሊዮን ሰዎች የሚናገር ቋንቋ ነው። በጥንታዊ ኢንካ መንግሥት መደበኛ ቋንቋ ነበረ። ዛሬም በቦሊቪያ ፔሩና አንዳንድ አውራጃ በኤክዋዶር መደበኛ ሁኔታ አለው። አይማራ የሚባለው ሌላ ደቡብ-አሜሪካዊ ቋንቋ ዘመድ ነው።

እስፓንያውያን ከወረሩ አስቀድሞ በሰፊ ይሰማ ሲሆን በዚያን ጊዜ ምንም ጽሕፈት አልነበረውም። ይሁንና መቆጣጠር ሲባጎዎች በማሰር ዘዴ ነበር የተፈጸመ። ዛሬ የሚጻፈው በላቲን ፊደል ነው።

ስዋሰው[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በቀችዋ ሦስት አናባቢዎች ብቻ አሉ እነሱም አ ኢ ኡ ናቸው።

ቁጥር
ነጠላ ብዙ
ተውላጠ ስም 1ኛ Ñuqa ኑቃ Ñuqanchik ኑቃንቺክ (ከነናንተ)

Ñuqayku ኑቃይኩ (ያለ እናንተ)

2ኛ Qam ቃም Qamkuna ቃምኩና
3ኛ Pay ፓይ Paykuna ፓይኩና

ቁጥሮች:- huk (1), iskay (2), kimsa (3), tawa (4), pichqa (5), suqta (6), qanchis (7), pusaq (8), isqun (9), chunka (10)

ግሦች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሙጫይ - መሳም
ሙጫኒ - እስማለሁ
ሙጫንኪ - ትስማለሽ / ትስሚያለሽ
ሙጫን - ይስማል / ትስማለች
ሙጫንቺክ - እንስማለን (እኔና እርስዎ)
ሙጫይኩ - እንስማለን (ያለእርስዎ)
ሙጫንኪቺክ - ትስማላችሁ
ሙጫንኩ - ይስማሉ
ሙጫርቃኒ - ሳምሁ (ሙጫርቃንኪ - ሳምክ ሳምሽ ወዘተ...)
ሙጫሳቅ - ወደፊት እስማለሁ
ሙጫስቃኒ - ስሜ ነበር

አብዛኛው አረፍተ ነገር የ'እርግጠኛነት ምልክት' ባዕድ መድረሻ አለው።

  • -ሚ እርግጠኛነት ወይም ዕውቀት ያመለክታል: Tayta Wayllaqawaqa chufirmi ታይታ ዋይላቃዋቃ ቹፊርሚ - አቶ ዋይላቃዋቃ ነጂ ነው (እኔ ራሴ አውቀዋለሁ)።
  • -ሲ የሚሰማ ወሬ ያመለክታል: Tayta Wayllaqawaqa chufirsi ታይታ ዋይላቃዋቃ ቹፊርሲ - አቶ ዋይላቃዋቃ ነጂ ነው (ስምቼ ነው)።
  • -ቻ ሊሆን የሚችል ወይም የሚሆን ምናልባትነት ያመለክታል: Tayta Wayllaqawaqa chufircha ታይታ ዋይላቃዋቃ ቹፊርቻ - አቶ ዋይላቃዋቃ ነጂ ይሆናል።
Wikipedia
Wikipedia