ቲታኖማኪያ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ቲታኖማኪያ (ግሪክ፦ Τιτανομαχία) ወይም «የቲታኖች ጦርነት» በጥንታዊ ግሪክ አፈ ታሪክ የ10 ዓመት የአማልክት ጦርነት ነበር። በአንዱ ወገን ክሮኖስቲታኖች ነበሩ፤ በሌላውም ዚውስና የኦሊምፑስ ወገን ነበረ።

ጦርነቱ የመጣበት ጠንቅ እንዲህ ይተረካል። ክሮኖስ አባቱን ኡራኑስ ሰለበውና ገድሎት ከንጉሥነት ገለበጠው። ኡራኑስ እየሞተ፣ ክሮኖስ በፈንታው በራሱ ልጆች እንዲገለበጥ የሚል ትንቢት ተናገረ። ከኡራኑስም ደም ጊጋንቴስ (ታላላቅ ወይም ረጃጅም ሰዎች) ተወለዱ።

የቲታኖኢች አለቃ ክሮኖስ አሁን ንጉሥ ሆኖ እኅቱን ሬያን ሚስት አደረጋት፤ ትንቢቱንም ለማምለጥ እያንዳንዱን ልጅ ስትወልዳቸው ክሮኖስ ቀጥታ በላቸው። ዚውስ ሲወለድ ግን እናቱ ሬያ ከክሮኖስ ሠወረችው አልተበላም። ሬያ ሕጻኑን ዚውስን ወደ ቀርጤስአማልጤያ አሳዳጊነት ላከችው። በኋላ ዚውስ ተመልሶ አባቱ ወንድሞቹን እንዲያስታውክ ልዩ መድኃኒት ይሠጣል። ከዚያ በኋላ ዚውስና ወንድሞቹ በቲታኖች ላይ በአመጽ ተነሡ።

የኔ መሣርያዎች

Variants
Actions
የማውጫ ቁልፎች
ጠቃሚ መሣሪያዎች
በሌሎች ቋንቋዎች