ትንኝ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
?ትንኝ
አደስ ኢጂብቲ፣ የቢጫ ወባ ተሸካሚ
አደስ ኢጂብቲ፣ የቢጫ ወባ ተሸካሚ
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: እንስሳ
ክፍለስፍን: አርትሮፖዳ
መደብ: በራሪ
ክፍለመደብ: ዲፕቴራ
ንኡስ ክፍለመደብ: ኔማቶኬራ
Infraorder: ከሊኮርሞፋ
ልእለ ዘመድ: ከሊኮይዳ

ትንኝ የዝንብ አይነት እንስሳ ናት። የትንኝ ሴቶች ተዋህስያን ስለሆኑ በደመ ሙቅ እንስሳቶች ላይ አርፈው፣ የእንስሳውን ቆዳ በሹል አፋቸው ከበሱ በኋላ፣ ምራቃቸውን ይረጩበታል። ይህን እሚያደርጉት የበሱት እንስሳ ደም እንዳይደርቅ ነው። በዚህ ሁኔታ ነገሮችን ካመቻቹ በኋላ፣ የአረፉበትን እንስሳ ደም ይመገባሉ ማለት ነው።

በሽታ የሚያጋቡት፣ ቆዳ ሲበሱ ወይንም ደም ሲመጡ ሳይሆን፣ ምራቃቸውን ሲረጩ ነው። ለዚህ ምክንያቱ በምራቃቸው ውስጥ አደገኛ ተውሳኮች ጎጆአቸውን ቀልሰው ስለሚኖሩ ነው[1][2]

ወንዶች ትንኞች የአበባ ጣዝማ ነው ምግባቸው። ሴቶቹም እንዲሁ የአበባ ጣዝማ ይመገባሉ፣ ሆኖም እንቁላል ሊጥሉ ሲሉ ብዙ ፕሮቲን ስለሚያስፈልጋቸው፣ የግዴታ ደም መምጠጥ አለባቸው። አለበለዚያ እንቁላል መጣል አይችሉም።


[ለማስተካከል] ማጣቀሻ

  1. ^ Harrison, Gordon A. 1978. Mosquitoes, malaria, and man: a history of the hostilities since 1880 ISBN 0525160256 / 0-525-16025-6
  2. ^ Day, Nancy 2001. Malaria, West Nile, and other mosquito-borne diseases Enslow. ISBN 9780766015975
የኔ መሣርያዎች

Variants
Actions
የማውጫ ቁልፎች
ጠቃሚ መሣሪያዎች
በሌሎች ቋንቋዎች