አልበርት አይንስታይን

ከውክፔዲያ
አልበርት አንስታይን እንደ አውሮጳዊያንን አቆጣጠር 1879 ዓ/ም የአይሁድ እምነት ተከያይ ለሆኑ ቤተሰቦች ጀርመን ውስጥ ተወለደ።በ1921 እ.ኤ.አ.

አልበርት አይንስታይን1895 ዓ.ም ነበር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንት ገብቶ በድግሪ ለመረቅ በስዊስ (ዙሪክ ከተማ) የምዝገባ ማመልከቻውን ያስገባው። ለአንስታይን ብቸኛ ማስረጃው በጀርመን ሙኒክ ከተማ የተማረበት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውጤቱ ብቻ ነበር። አባቱ በሙኒክ ከተማ የከፈተው ንግድ ለኪሳራ በመዳረጉና ወደ ጣሊያን ሀገር በመሰደዱ የተነሳ ጀርመን ሀገር ብቻውን የቀረው አይንስታይን እንደ ድሮው ለትምህርቱ ትኩረት መስጠት አልሆነለትም። በዚህ ወቅት ነበር አይንስታይን ትምህርቱን አቋርጦ በሚላን ከሚገኙት ቤተሰቦቹ ጋር የተቀላቀለው።

ከጣሊያን ወደ ስዊስ በመሄድ በኮሌጅ ደረጃ ገብቶ ለመመረቅ ያመላከተበት የስዊስ «ዙሪክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጂ» ምንም እንኳን አይንስታይን ትምህርቱን ያላጠናቀቀ ቢሆንም የመግቢያ ፈተናውን ካለፈ ሊማር እንደሚችል ተፈቀደለት። አይንስታይንም በታላቅ ወኔ በማትሪክ ውጤታቸው ከፍተኛ ነጥብ ካመጡና በዕድሜ ከሜበልጡት ተማሪዎች ጋር ወደፈተና አዳራሹ ገባ።

የፈተናው አይነት አለም አቀፍ ይዘት ያላቸው እንደ «ፈረንሳይኛሒሳብፊዚክስታሪክጆግራፊሙዚቃ» ይገኙበታል። የመግቢያ ፈተናዎቹም ለኢንጅነሪንግ ትምህርት የሚማሩ ተማሪዎችን ብቃት በሚገባ አብጠርጥረው ሊፈትኑ የሚችሉ ጥያቄዎችን ያካተተ ነበር። ይህን ከባድ ፈተና ነበር አይንስታይን የተጋፈጠው። አንድ ሳምንት የፈጀው ይህ የመግቢያ ፈተናም በሶሥተኛው ሳምንት ነበር ውጤቱ የተገለጨው።

ከ300 ተማሪዎች ውስጥም በዲግሪ ፕሮግራም እንዲታቀፉ የሚፈቀድላቸው ከመቶ ለማይበልጡት በመሆኑ ፍክክሩ እጅግ ከባድ ነበር። የተፈታኝ ተማሪዎችም ውጤት አንድ አንድ እያል መለጠፍ ተጀመረ ከማትስና ከፊዚክስ የሰቃዮች ሰቃይ የነበረው አንስታይን ነበር። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያቋረጠው፣ የማትሪክ ፈተና ያልወሰደው አንስታይን በማትሪክ ውጤታቸው አንቱታን ያተረፉ የሲውዘር ላንድ ተማሪዎችን ከእግሩ ስር አሰልፏቸዋል። ይሁን እንጂ ይህን መሰሉ የሰቀላ ውጤት በሌሎች የትምህርት አይነቶች ላይ ሊደግም ግን አልተቻለውም ነበር። አልበርት አንስታይን ተወልዶ ያደገው በጀርመን ነው ፈረንሳይኛን ቋንቋ መሆኑን ከማወቅ የዘለለ እውቀት አልነበረውም። በሰዎች ትልቅ ግምት የሚሰጣቸው አለባበስና ፀጉር አበጣጠር በእርሱ ዘንድ ተራ ነገሮች ናቸው። ፀጉሩም ቢሆን ሁሌም ጨፍራራ ነበር። ብሎም የምርምር ስራዎቹን ወደ እንግሊዘኛ የሚለውጡለት ጓደኞቹ ነበሩ። ብሎም ልታሪክ ትምህርትና ለጂኦግራፊ ትምህርት ንቁ ስላልነበር ወደ ኮሌጅ ለመግባት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀረ።

በፈተና መውደቁን የሰሙት አባቱ ሄርማን እና እናቱ ፓውሊን አንስታይንን በቶሎ ወደ ሚላን እንዲመጣ አደረጉት። በአንድ በኩል ልጃቸው ትምህርቱን እንዲያጠናቅቅ ቢመክሩትም አሻፈረኝ ብሏችው ነበርና ብዚህ ሁኔታ መቆየቱ አሳስቧችዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ከዙሪክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሰናበቱ አሳዝኗቸዋል። በመጨረሻ አንስታይን ጉዞውን ከሲውዘር ላንድ ወደ ጣሊያኗ ሚላን አደረገ። ከወላጆቹም ጋር ተገናኘ። ወላጆቹም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በሚላን እንዲያጠናቅቅ ቢመክሩትም እሱግን አሻፈረኝ አለ። አሁንም ምኞቱ ያለው በታላቁ የዚውዘርላንድ ኮሌጅ (ዙሪክ ፖሊ ቴክኒክ) ላይ እንደሆነ በጠንካራ አንደበቱ ገለፀላቸው። አንስታይንን እንደገና ወደ ሲውዘርላንድ ላኩት። አንስታይን አሁን አንድ ነገር ማድረግ እንዳለበት አላጣውም። በዚህ ኮሌጅ ገብቶ ለመማር የመግቢያ ፈተናውን ማለፍ ይጠበቅበታል። ፈተናውን በሚገባ ለማለፍ ደግሞ የሁለተኛ ድረጃ ትምህርቱን ማጠናቅቅ እንዳለበርት ተገንዝቧል። በመሆኑም ከዙሪክ ከተማ ብዙም ወደማትርቀው አይራው ከተማ አመራ። በአይራው ከተማ ውስጥ በምትገኘው የካንቶሊክ ት/ቤት ተመዝግቦ ያቃረጠውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ቀጠለ። በዚህ ት/ቤት ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ስኬት ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ትምህርቱን አጠናቀቀ። በ1986 አንስታይን በዙሪክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ገብቶ ለመማር የሚያስችለውን ፈተና እንደገና ወሰደ። "ከትላንት እንማራለን፣ ዛሬን እንኖራለን፣ ስለነገም ተስፋ እናደርጋለን" የሚለው አንስታይን በመጨረሻ ህልሙን እውን አድርጎ በኮሌጁ ለመታቀፍ በቃ። የኮሌጅ ቆይታው በጣም አስገራሚ የነበረ ሲሆን ብዙ ጊዜውንም ክፍል ገብቶ ከመማር ይልቅ በቤተ-ሙከራ ጅፍሎች ውስጥ ማሳለፍ ይመርጥ ነበር። ገና ኮሌጅ በገባ በመጀመሪያው ሴሜስተር ላይ ሳይንሳዊ ጥናት በማካሄድ አድናቆትን ያገኘው አንስታይን የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርትን የሚያፈቀረው ለንድፈ ሃሳብ (ቴዮሪ) ሳይሆን ለተግባራዊ አጠቃቀም ነበር። በርግጥ አንድ ተግባራዊ ውጤት ያለውን ሳይንሳዊ ጥናት ላማካሄድ ቲዮሪ መሰረታዊ መነሻ ማሆኑ አይካድም አንስታይን ግን 10 በመቶ ጊዜውን ለጥናት 90 በመቶውን ደግሞ ለተግባራዊ ምርምር ነበር የሚያውለው። የ16 አመት ልጅ ግሩም የሳይንስ ምርምር አደረገ ሲባል ቢደመጥ ማን ያምናል። ነገሩ ግን እውነት ነው አንስታይን በ16 አመቱ ነበር ኢተር በማግኔት መግነጢሳዊ ሃይል ውስጥ ሲያልፍ የሚኖረውን ባህሪይ ያጠናው። በዚያው ኮሌጅ ውስጥ የተለያዩ ሽልማቶን የተቸረው አንስታይን ነበር። በ1890 የኮሌጁ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆን የኤልክትሪክ ምህንድስና ድግሪውን ጫነ። በመረቃው ወቅት የደስታው ተካፋይ በመሆን ከሚላን ተነስተው ዙሪክ የደረሱት እናቱ ፓውሊን አባቱ ሄርማን ደስታቸው እጅግ ሀያል ነበር። አብራው ደግሞ አንዲት የሲውዘርላንድ ዜግነት ያላት ተመራቂ ትገኛለች። ሜሊቫ ሜሪክ በመባል የምትጠራው ይህቺ ወጣት ከአንስታይን ጋር ስትማር የነበረችና ትምህርት ያገናኛቸው ፍቅረኛሞች ናቸው። የአንስታይን የእድሜ ልክ ጓደኛ የነበረው ኢንጂነር ማይክል ቢሶ የተገኘው ከዚሁ ኮሌጅ ነው። የምረቃ ስነ-ስርአቱ አምሮና ደምቆ ኢንጂነር አልበርት አንስታይንም ካባና ወርቁን አጥልቆ ነበር የተጠናቀቀው። ቀሪው ምርቃት ደግሞ የተካሄደው በሜሊቫ ሜሪክ ቤተሰቦች ውስጥ ነበር።