ዓረብኛ

ከውክፔዲያ
(ከአረብኛ የተዛወረ)
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አረንጓዴ: አረብኛ ብቻ መደበኛ ነው። ሰማያዊ: አረብኛ ከመደበኛ ቋንቋዎች አንዱ ነው።

ዓረብኛ (العربية) የሴማዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ሆኖ የዕብራይስጥአረማያ እንዲሁም የአማርኛ ቅርብ ዘመድ ነው። 250 ሚሊዮን የሚያሕሉ ሰዎች እንደ እናት ቋንቋ ይችሉታል፤ ከዚህም በላይ በጣም ብዙ ሰዎች እንደ 2ኛ ቋንቋ ተምረውታል። የሚጻፈው በአረብኛ ፊደል ነው። በአረብ አለም ውስጥ አያሌ ቀበሌኞች ይገኛሉ።

ቋንቋው በእስልምና ታላቅ ሚና አጫውቷል። እስላሞች አላህ ለሙሐማድ ቁርዓንን ሲገልጽ በአረብኛ እንደ ሆነ ስለሚያምኑ እንደ ቅዱስ ቋንቋ ይቆጥሩታል። አብዛኛው አረብኛ ተናጋሪዎች ሙስሊሞች ናቸው።

ዛሬ በምዕራብ ዓለም ደግሞ ብዙ ሰዎች አረብኛ እያጠኑ ነው። በታሪክ ከፍተኛ ሚና በማጫወቱ መጠን፤ ብዙ የአረብኛ ቃላት ወደ ሌሎች ቋንቋዎች ገብተዋል።