አይሳክ ኒውተን

ከውክፔዲያ

ሰር አይሳክ ኒውተን ከ[[ጃንዩዌሪ] 4 ቀን [[1663 እ.ኤ.አ.] እስከ ማርች 31 ቀን 1727 እ.ኤ.አ. የኖረ እንግሊዛዊፊዚክስ፤ የሒሳብ፤ የስነ ክዋክብት፤ የስነ መለኮት፤ የተፈጥሮአዊ ፍልስፍና እና ጥንት የነበረው የአልኬሚ ምሁር ነበረ። ምናልባትም ኒውተን በጣም ከሚታወቅባቸው ነገሮች ውስጥ ሶስቱ የኒውተን ሥነ-እንቅስቃሴ ህጎች ፤ የኒውተን የግስበት ቀመርካልኩለስ ለተባለውን የሒሳብ ክፍል መጀመር (ይህን ክብር ከጀርመናዊው ምሁር ከጎትፍሪድ ሌብኒትዝ ጋር ይጋሩታል)፤ ስለ ብርሃንና ስለሚይዛቸው ቀለማት ያገኘው ግኝት ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም ኒውተን የእንቅስቃሴ ህጎችን በመጠቀም የፕላኒቶች (ፈለገ ሰማያት) እንቅስቃሴ በነዚሁ ህጎች እንደሚመሩ በማሳየት እና የሌላ ምሁር የጃናንስ ኬፕለር የፕላኒቶች እንቅስቃሴ ህግ ጋር እንደሚጣጣም በማሳየት ፤ በፊት ይታመንበት የነበረውን መሬት የሁሉም ነገሮች ማዕከል ናት የሚባለውን ሐሳብ ትክክል እንዳልሆነ በሳይንሳዊ መንገድ አሳይቷል።

የህይወት ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሰር አይሳክ ኒውተን በ4ኛ ቀን 1642 አመተ ምህረት ተወለደ። አባቱ ከመወለዱ በፊት በመሞቱ እናቱ ከሌላ ባል ጋር ኮበለለች። ስለዚህ ከአያቱ ጋር መደግ ጀመረ። ከ 12-10 አመት ድረስ ኒውተን በግራንተም ግራመር ት/ቤት ውስጥ ተማረ። ኒውተን ገበሬ መሆን ባለመፈለጉ ወደ ተሪኒቲ ኮሌጅ ካምበሪጅ ገባ። ዲግሪውን በ፩፮፭፱ ጨረሰ። ነገር ግን በ፩፮፮፮ በነበረው ወረርሽ ምክንያት ከኮሌጁ መሰደድ ነበረበት። በቀጣዩ አመት ተመለሰ። በቀጣዮቹ አመታት ስለ ሥነ-እንቅስቃሴ ህጎች፣ ካልኩለስ እናም ስለ ነጭ ብርሃን እና ስለሚይዛቸው ቀለማት ያገኘው ግኝት ይጠቀሳሉ። በማርች ፫፩ ቀን ፩፯፪፯ ከዚህ አመት በሞት ተለየ ኒውተን ራሳቸውን በቀላሉ ከሚገልጹ ተመራማሪዎች አንዱ ነበር።።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Isaac Newton የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።