እስክንድርያ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
እስክንድርያ
Alexcoast.jpg
የእስክንድሪያ ወደብ
ኗሪ ስም Ⲣⲁⲕⲟⲧⲉ Rakotə
አገር ግብፅ
ክፍለ ሐገር እስክንድርያ
የሕዝብ ቁጥር 4,110,015
እስክንድርያ is located in ግብፅ
{{{alt}}}
እስክንድርያ
እስክንድርያ፣ ግብፅ

ኬክሮስና ኬንትሮስ
31°12′ ሰሜን ኬክሮስ እና 29°55′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


እስክንድርያ ወይንም አሌክስዳንድርያ331 ዓክልበ.ታላቁ እስክንድር የተመሰረተች የጥንቱ ዘመን ታላቅ ከተማ ነበረች። በግብጽ አገር በግሪኮች የተመሰረተችው ይች የባህር ጠረፍ ከተማ በዘመኑ በምድር ላይ ከነበሩት ሁሉ ታላቅ የነበረውን የእስክንድርያ ቤተ መጻሕፍት በመያዝ ትታወቃለች። ስለሆነም ብዙ ስማቸው እስካሁን የሚጠሩ የግሪክ ተመራማሪዎች በዚች ከተማ ኖረዋል። ታዋቂው የጂዎሜትሪ ተማሪ ዩክሊድ በዚች ከተማ ይኖር እንደነበር ይጠቀሳል። በሌላ ጎን የጥንቱ ዘመን አለም አቀፍ አሰድናቂ የሚባለው የባህር ፋኖስ በዚሁ ከተማ ይኖር ነበር። እስክንድርያ፣ ከተቆረቆረ ጀምሮ ለሚቀጥሉት 1000 ዓመታት የግብፅ ዋና ከተማ በመሆን አገልግሏል። በኋላ ግብጽ በመስሊሞች ስትወረር ዋና ከተማው ወደ ፉስታት ካይሮ ተዛወረ።

Alexandria panorama.jpg