እዚያም ቤት እሳት አለ

ከውክፔዲያ

እዚያም ቤት እሳት አለ

(17) አለቃ የጎረቤት ፍቅር ይጀምሩና ባለቤታቸው ወ /ሮ ማዘንጊያ ዉኃ ሊቀዱ ሲወርዱ ጎረቢት ፍቅርን ልትቃመስ ትመጣለች። መጥታም ከአለቃ ጋር ሲንጎዳጎዱ ሳያስቡት ወ /ሮ ማዘንጊያ ቢደርሱባቸው ውሽምዬም ከመደንገጧ የተነሳ ልጅዋን ያነሳች መስሏት ያለቃን ልጅ አንጠልጥላ ትሮጣለች። ነገሩ የገባቸው ማዘንጊያም ልጁን አንስተው «አሁን እዚህ እሳት ውስጥ ልክተተው?» ቢሏቸው አለቃም ማዘንጊያ እዚያም ቤት እሳት አለ ብለው ልጁን አተረፉ አሉ።