ኮፕንሀገን (København) የዴንማርክ ዋና ከተማ ነው።
ከተማው መጀመርያው የተሠራው በ11ኛው ክፍለ ዘመን ነበር። ስሙ ከጥንታዊ ዳንኛ ሲሆን ትርጉሙ 'ነጋዴዎች ወደብ' ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 1,094,400 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 55°43′ ሰሜን ኬክሮስ እና 12°34′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።