ወደ ሮማውያን ፲፫

ከውክፔዲያ
ወደ ሮማውያን ፲፫
በ፫ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ ወደ ሮማውያን ፲፪ - ወደ ሮማውያን ፲፫ በኮዴክስ ካሮሊነስ
አጭር መግለጫ
ፀሐፊ ጳውሎስ
የመጽሐፍ ዐርስት ወደ ሮማውያን
የሚገኘው በአዲስ ኪዳን ፮ኛው መጽሐፍ
መደብ የጳውሎስ መልዕክት


ወደ ሮማውያን በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው መልዕክት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ እያለ በ፶ ዎቹ ዓ.ም. የጻፈው መልዕክት ነው ። ይህ ምዕራፍ ፲፫ ሲሆን በ፲፬ ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል ። ጳውሎስ በዚህ መልዕክቱ በተለይ (ቁ ፩ - ፯)፣ ማዘዝና መታዘዝ ፣ በመንፈሳዊ መንገድ ዓላማውንና ትርጉሙን ያስረዳል ። እንደምናውቀው ግን ብዙ መንግሥታት ይህን መልክት ለራሳቸው እንዲመች አርገው ተርጉመው በሕገመንግሥታቸው ውስጥ አስገብተው ተጠቅመውበታል ።


ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን መልዕክቱን የጻፈበት ምክኒያት አይሁዳውያንና ሮማውያን በሰላም አንድላይ በሮም ለብዙ ዘመን ሲኖሩ ቆይተው ክርስትና በተመሠረተበት ወቅት ፣ አይሁዳውያን ክርስቶስ እኛን ነው የመረጠን ለመንግሥቱ እናንተን አይደለም... ሲሊ ሮማውያን ደግሞ እናንተ ሰቀላችሁት እንጂ ምን አረጋቹህለት... እየተባባሉ እርስበርሳቸው ጥል ስለፈጠሩ እነሱን ለማስታረቅ ጻፈው ።

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮማውያን ምዕራፍ ፲፫

ቁጥር ፩ - ፲፬[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

1፤ነፍስ፡ዅሉ፡በበላይ፡ላሉት፡ባለሥልጣኖች፡ይገዛ።ከእግዚአብሔር፡ካልተገኘ፡በቀር፡ሥልጣን፡ የለምና፤ያሉትም፡ባለሥልጣኖች፡በእግዚአብሔር፡የተሾሙ፡ናቸው። 2፤ስለዚህ፥ባለሥልጣንን፡የሚቃወም፡የእግዚአብሔርን፡ሥርዐት፡ይቃወማል፤የሚቃወሙትም፡በራሳቸው፡ላይ፡ ፍርድን፡ይቀበላሉ። 3፤ገዢዎች፡ለክፉ፡አድራጊዎች፡እንጂ፥መልካም፡ለሚያደርጉ፡የሚያስፈሩ፡አይደሉምና።ባለሥልጣንን፡እንዳትፈራ፡ትወዳለኽን፧መልካሙን፡አድርግ፡ከርሱም፡ምስጋና፡ይኾንልኻል፤ 4፤ለመልካም፡ነገር፡ለአንተ፡የእግዚአብሔር፡አገልጋይ፡ነውና።በከንቱ፡ግን፡ሰይፍ፡አይታጠቅምና፡ክፉ፡ ብታደርግ፡ፍራ፤ቍጣውን፡ለማሳየት፡ክፉ፡አድራጊውን፡የሚበቀል፡የእግዚአብሔር፡አገልጋይ፡ነውና። 5፤ስለዚህ፥ስለ፡ቍጣው፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥ስለ፡ኅሊና፡ደግሞ፡መገዛት፡ግድ፡ነው። 6፤ስለዚህ፡ደግሞ፥ትገብራላችኹና፤በዚህ፡ነገር፡የሚተጉ፡የእግዚአብሔር፡አገልጋዮች፡ናቸውና። 7፤ለዅሉ፡የሚገ፟ባ፟ውን፡አስረክቡ፤ግብር፡ለሚገ፟ባ፟ው፡ግብርን፥ቀረጥ፡ለሚገ፟ባ፟ው፡ቀረጥን፥መፈራት፡ ለሚገ፟ባ፟ው፡መፈራትን፥ክብር፡ለሚገ፟ባ፟ው፡ክብርን፡ስጡ። 8፤ርስ፡በርሳችኹ፡ከመዋደድ፡በቀር፡ለማንም፡ዕዳ፡አይኑርባችኹ፥ሌላውን፡የሚወድ፡ሕግን፡ፈጽሞታልና። 9፤አታመንዝር፥አትግደል፥አትስረቅ፥በውሸት፡አትመስክር፥አትመኝ፡የሚለው፡ከሌላዪቱ፡ትእዛዝ፡ዅሉ፡ ጋራ፡በዚህ፦ባልንጀራኽን፡እንደ፡ነፍስኽ፡ውደድ፡በሚለው፡ቃል፡ተጠቅሏ፟ል። 10፤ፍቅር፡ለባልንጀራው፡ክፉ፡አያደርግም፤ስለዚህ፥ፍቅር፡የሕግ፡ፍጻሜ፡ነው። 11፤ከእንቅልፍ፡የምትነሡበት፡ሰዓት፡አኹን፡እንደ፡ደረሰ፡ዘመኑን፡ዕወቁ፤ካመን፟በ፟ት፡ጊዜ፡ይልቅ፡መዳናችን፡ ዛሬ፡ወደ፡እኛ፡ቀርቧልና። 12፤ሌሊቱ፡ዐልፏል፥ቀኑም፡ቀርቧል።እንግዲህ፡የጨለማውን፡ሥራ፡አውጥተን፡የብርሃንን፡ጋሻ፡ጦር፡ እንልበስ። 13፤በቀን፡እንደምንኾን፡በአገባብ፡እንመላለስ፤በዘፈንና፡በስካር፡አይኹን፥በዝሙትና፡በመዳራት፡ አይኹን፥በክርክርና፡በቅናት፡አይኹን፤ 14፤ነገር፡ግን፥ጌታን፡ኢየሱስ፡ክርስቶስን፡ልበሱት፤ምኞቱንም፡እንዲፈጽም፡ለሥጋ፡አታስቡ።

ትኩረት የሚገባቸው መልዕክት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ቁጥር ፩ - ፯
  • ቁጥር ፱
  • ቁጥር ፲፩ - ፲፬
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Bible የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።