የሞንጎላውያን መንግሥት
የሞንጎላውያን መንግሥት ከ1198 እስከ 1286 ዓም. ድረስ የተባበረ መንግሥት ነበረ።
በ1198 ዓም መጀመርያው ንጉሥ ቺንግስ ካን የሞንጎላውያን ብሔሮች በሞንጎልያ በአንድ መንግሥት አዋሃዳቸው። በዚህም ዘመን ያህል በቻይና የእጅ መድፍ እየተደረጀ ነበር። ሞንጎላውያን ይህን ቴክኖሎጂ አገኝተው በዚያው ምክንያት ሥራዊታቸው ባሩድ ባልታወቀባቸው አገራት ወርረው እንዳልተሸነፉ ይሆናል። መንግሥታቸው በፍጥነት ከአውሮፓ እስከ ቬትናም ድረስ ይስፋፋ ቻለ።
ችንግስ የአረመኔነት ተከታይ ቢሆንም፣ በሞንጎላውያን በኩል ሃይማኖቶች ሁሉ - በተለይም ክርስትና፣ ቡዲስም፣ እስልምና - ይገኙ ነበርና ይከብሩ ነበር። ዳሩ ግን ሞንጎሎች ለእስላም ወይም ለአይሁድ የራሳቸውን በግ እንዲያርዱ ወይም የራሳቸውን ምግብ አልፈቀዱላቸውም ነበር፤ ሰው ሁሉ እንደ ሞንጎላውያን እንዲመገቡ አስገደዳቸው። ይህም እንስሳው የሚታርደው በጉሮሮ በመቋረጥ ሳይሆን በአረመኔ መንገድ ልቡ በሕይወት ሳለ በእጅ መጨመቅ ነበር። ቺንግስ ደግሞ የዳዊስም አለቃ ጪው ቹጂ ለመንግሥቱ ሁሉ ሃይማኖታዊ አለቃ እንዲሆን አንዴ ሾመው። ችንግስ እራሱ ግን የአረመኔ ጣኦት ተንግሪ ተከታይ ሆኖ ቀረ። የሞንጎላውያን ሕገ መንግሥት ወይም «ያሣ» በምስጢር የተደበቀው ሰነድ ስለ ሆነ፣ አሁን በከፊል ብቻ ይታወቃል።
ከ1286 ዓም. በኋላ፣ መንግሥቱ በመጨረሻነት በአራት መንግሥታት ተከፋፍሎ ነበር፦
- ወርቃማ መዓት - በስሜን- ምዕራብ፣ በ1251 ዓም ተገነጠለ
- ኢልኻናት - በደቡብ- ምዕራብ (ፋርስ)፤ በ1251 ዓም ተገነጠለ
- ጫጋታይ ግዛት - በመካከላቸው፣ በ1258 ዓም ተገነጠለ
- ይዋን ሥርወ መንግሥት - በቻይና፣ 1271 ዓም ተመሠረተ።
ከነዚህም መሃል፣ መጀመርያ ሦስቱ መንግሥታት በኋላ እስላማዊ ሆኑ፣ አራተኛውም (የይዋን ሥርወ መንግሥት በቻይና) ቡዲስት ሆነ።