የብረት ማዕድኖች

ከውክፔዲያ

ብረታ ብረቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]


የብረት ማዕድናት በሁለት ይከፈላሉ። እነሱም ፕሪሽየስ ሜታል መደብ እና ቤዝ ሜታል መደብ ናቸው።

ወርቅ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኮሞዲቲ ስም የመገበያያው ስም የገበያ ቦታ ስም በኮንትራክት (ውል) መጠን የክብደት/ብዛት መጠን
ወርቅ - ጎልድ
GC

YG
COMEX  ኒውዮርክ መርከንታይል ኤክስቼንጅ

CME  ቺካጎ መርከንታይል ኤክስቼንጅ
1

1
100 ትሮይ አውንስ

33.2 ትሮይ አውንስ



ወርቅ (እንግሊዝኛ gold /ጎልድ/) ለብዙ አመታት ዋጋውን በከፍተኛ ደረጃ መጠን ጠብቆ ያለ ሲሆን ተፈላጊነቱም በገበያተኞች ዘንድ ቀንሶ አያውቅም። ከብዙ አገሮች የገንዘብ መተመኛንት እስከ ግለሰቦች ጌጣጌጥነት ድረስ ለረጀም ጊዜያት ግልጋሎቱን ሲያበረክት የቆየና ተፈላጊነትም ያለው የብረት ማዕድን ነው።

ወርቅ እንደ ሌሎቹ የብረታ ብረት ማዕድኖች የይዘቱ ሚዛን የሚለካው በትሮይ አውንስ መጠን ነው። አንድ ትሮይ አውንስ ፤ ሠላሳ አንድ ነጥብ አስር ግራም ነው። ትሮይ የሚባለውን ስም ያገኘው ከግሪክ አገር ሳይሆን ፤ በፈረንሳይ አገር ከሚገኘው ከዘመናት በፊት የወርቅና የብር እንዲሁም የተለያዩ የከበሩ ማዕድናት ይሸጥበት ከነበረው ትሮይስ ከተማ ነው።

ብዛት ያለው ወርቅ ሲሸጥና ሲገዛ በሜትሪክ ቶንስ የሚዛን መጠን ነው። አንድ ሜትሪክ ቶን ወርቅ ከሠላሳ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ ትሮይ አውንስ ጋር እኩል ነው። ይህም ማለት ፣
አንድ ሜትሪክ ቶን ወርቅ = ሠላሳ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ ትሮይስ አውንስ ወርቅ ነው።
የወርቅ ጌጥ ማድረግ ለሚወዱ ሰዎች ደግሞ ፤ የንፁህ ወርቅ መጠን በካራት ይለካል። በጣም ንፁህ የሆነው ሃያ አራት ካራት ሲሆን ከዚያ ዝቅ ያለ መጠን ያለው ደግሞ ከሌላ ብረት ማዕድን ጋር የተደባለቀው ነው። የዋጋውም ዓይነት በዚሁ መጠን በወርቅ ሰሪ ቤቶች ሱቅ ውስጥ ይለያያል።

ኮሞዲቲ ገበያ ውስጥ ወርቅ የሚገዛውና የሚሸጠው በኮንትራት መልክ ሲሆን መጠኑም አንድ ኮንትራት በአንድ መቶ አውንስ ወርቅ ነው። ይሄም ማለት አንድ የወርቅ ኮንትራት እኩል የሚሆነው ሠላሳ አንድ ነጥብ አስር ግራም ሲባዛ በአንድ መቶ ነው። ውጤቱን ወደ ግራምና ወደ ኪሎግራም ለማወቅ ያክል ማግኘት ቢቻልም የኮሞዲቲ መገበያያ መጠኑ በኮንትራት ቁጥር ብዛትና በትሮይ አውንስ ክብደት መለኪያ ነው።

የወርቅ ኮንትራት የሚሸጡባቸው ቦታዎች ሁለት የመገበያያ ዓይነት አላቸው። አንደኛው የኒውዮርኩ ፤ አንድ ኮንትራት በአንድ መቶ ትሮይ አውንስ ሲሆን ፤ ሁለተኛው ደግሞ ቺካጎ ውስጥ አንድ ኮንትራት በሠላሳ ሦስት ነጥብ ሁለት ትሮይ አውንስ ነው። የገበያ ምልክት ፊደላቸው ጂ ሲ GC ለባለ አንድ መቶ ትሮይ አውንሱ ኮንትራክት እና ዋይ ጂ YG ለ ባለ ሠላሳ ሦስት ነጥብ ሁለት ትሮይ አውንስ ነው።


ብር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኮሞዲቲ ስም የመገበያያው ስም የገበያ ቦታ ስም በኮንትራክት (ውል) መጠን የክብደት/ብዛት መጠን
ብር - ሲልቨር
SI

YI
COMEX  ኒውዮርክ መርከንታይል ኤክስቼንጅ

CME  ቺካጎ መርከንታይል ኤክስቼንጅ
1

1
5000 ትሮይ አውንስ

1000 ትሮይ አውንስ



ብር ፤ እንግሊዝኛ silver /ሲልቨር/ የተባለው ማዕድን ደግሞ ተፈላጊነቱ በድሮ ጊዜ ለመገበያያነት ቀጥሎም ለተለያዩ የንብረት እቃዎችና የፋብሪካ ውጤቶች አገልግሎቱን የሚሰጥ የማዕድን ብረት ነው። ንፁህ ብር የሚባለው ብዙውን ጊዜ ዘጠና ሁለት ነጥብ አምስት ያክሉን ሲልቨር የሚይዘው ነው። የተቀረው ሰባት ነጥብ አምስት ከመዳብ (ኮፕር) - ወይንም ከሌላ የብረት ማዕድን ጋር የሚደባለቀው ነው። የአጠቃላይ ስሙም እስተርሊንግ ሲልቨር ይባላል። መደባለቁ የሚጠቅመው የብር ይዘቱን ለማጠንከር ወይንም በቀላሉ ከውስጡ ያሉትን ንጥረ ማዕድኖች በሙቀት ጊዜ ወይንም በቅዝቃዜ መጠናቸው እንዳይለወጥ ነው።

በኮሞዲቲ ገበያ ውስጥ በሚሸጥበትና በሚገዛበት ጊዜ በሁለት መመዘኛ መልክ ነው። አንደኛው በአምስት ሺህ ትሮይ አውንስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በአንድ ሺህ ትሮይ አውንስ ነው። የንግድ መገበያያ ምልክታቸውም- ኤስ አይ SI - ለባለ አምስት ሺህ ትሮይ አውንስ ሲሆን -ዋይ አይ YI- ደግሞ ለባለ አንድ ሺህ ትሮይ አውንስ ነው።


ፕላቲንየም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]


የኮሞዲቲ ስም የመገበያያው ስም የገበያ ቦታ ስም በኮንትራክት (ውል) መጠን የክብደት/ብዛት መጠን
ብር - ሲልቨር
PL
NYMEX  ኒውዮርክ መርከንታይል ኤክስቼንጅ
CME ቺካጎ መርከንታይል ኤክስቼንጅ
1
50 ትሮይ አውንስ





መዳብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]


የኮሞዲቲ ስም የመገበያያው ስም የገበያ ቦታ ስም በኮንትራክት (ውል) መጠን የክብደት/ብዛት መጠን
መዳብ  -  ኮፐር<
CAD

HG
LME  ለንደን ሜታል ኤክስቼንጅ

CME/COMEX  ቺካጎ መርከንታይል ኤክስቼንጅ
1

1
25 ቶን

25000 ፓውንድ