የዓመፅ ኑዛዜ

ከውክፔዲያ

የዓመፅ ኑዛዜ በደራሲ አቤ ጉበኛ በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. የተፃፈ ሲሆን 85 ገጾች አሉት። በመፅሐፉም የተገለፀው ታሪክ ሰፊ ሆኖ ደራሲው ባጭሩ ለመግለፅ ቀላልና አጭር በሆነ ዘዴ የፃፈው ነው።

ታሪኩም አንድ ራሱን ወዳድ ሰው ታሪክ በኑዛዜ መልክ የሚገለፅበት ሲሆን፣ በአንድ የገጠር መንደር ውስጥ ጥሩ ኑሮ አላቸው ከሚባሉ ቤተሰቦች ውስጥ የወጣው ባለታሪክ ቤተሰቦቹን በድንገተኛ ህመምወያጣል። በድንገትም ያልተጠበቀ የቤተሰብ መበታተን ይደርሳል። በአጎቱ ሚስት ይፈፀምበት በነበረው ድርጊት ተማሮ ወደ ከተማ የኮበለለው ወጣት ባገኘው የትምሀርት ዕድል ተጠቅሞ አገሩንና ወገኖቹን መርዳትና መንከባከብ ሲገባው በተለያዩ ክፉ ነገሮች ተጠምዶ ይልቁንም በአልጠግብ ባይነት ከሚገባው በላይ ሃብት በማግበስበስና የወገኖቹንም ድርሻ ጭምር በመስበሰብ ለአገሩም ሆነ ለወገኖቹ የተጣለበትን ተስፋ ሳይፈፅም በሞት አፋፍ ላይ ሳለ የሚሰማውን ፀፀትና እሱን አይተው ሌሎች እንደ እርሱ ከመሆን እንዲቆጠቡ የሚናገርበት ሲሆን በተጨማሪም የርሱ ህይወት ትምህርት እንዲሆናቸው በመጨረሻም ሲበድላቸውና ሲያሳዝናቸው ለኖሩት ወንድሞቹና እንዲሁም ለወገኑ የሚያስተላልፈውን የኑዛዜ ቃል የምናይበት ነው።

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]