ፖርቶፕሪንስ

ከውክፔዲያ

ፖርቶፕሪንስ (ፈረንሳይኛ፦ Port-au-Prince /ፖርት-ኦ-ፕረንስ/፤ ክረዮል፦ Pòtoprens /ፖቶፕወንስ/) የሀይቲ ዋና ከተማ ነው።

ፖርት ኦ ፕሪንስ

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 1,764,000 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 1,119,000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 18°32′ ሰሜን ኬክሮስ እና 72°20′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

በ1650 ዓ.ም. አካባቢ፣ ፈረንሳዊ ዘራፊ መርከበኞች ሠፍረው አንድ ሆስፒታል (ሀኪም ቤት) ሰርተው የዙሪያውን ስም 'ኦፒታል' (ሆስፒታል) አሉት። ከተማው የተመሠረተ በ1741 ዓ.ም. ሲሆን በ1762 ዓ.ም. የቅኝ አገሩ መቀመጫ ወደዚያ ከካፕ-ፍራንሴ (የዛሬው ካፕ-አይስየን) ተዛወረ። ከ1783 እስከ 1796 ዓ.ም. በሃይቲ አብዮት ጊዜ ስሙ ፖርት ሬፑብሊካን ነበረ።