Jump to content

ኩንታል

ከውክፔዲያ

ኩንታል ማለት አሁን በተለምዶ የአንድ መቶ ኪሎግራም ክብደት መለኪያ ነው። በተለይ የእህል ምርት መለኪያ ነው።

የስሙ «ኩንታል» ታሪክ በተዘዋዋሪ መንገድ መጥቷል።

በአብዛኞቹ አገራት ዛሬ «ኩንታል» ለመቶ ኪሎ ክብደት ይጠቀማል፣ ለምሳሌ ኢትዮጵያሕንድአልባኒያፈረንሳይእስፓንያዩክራይንቸኪያኢንዶኔዥያ

ፖርቱጋል ኩንታል ግን እንዲሁም የዶሚኒካን ሪፐብሊክ ኩንታል 58 ኪሎ ያህል ነው።

ብዙ ሌሎች አገራት ከሮማይስጥ centenarius በሌላ መንገድ የመጣ ቃል centner /ሰንትነር/ ይጠቅማሉ። በፖልኛስዊድኛ፣ በኦስትሪያስዊስ አገር እና በቀድሞ ሶቭየት ኅብረት አገራት፣ ይህ ቃል (ጸንትነር / ሰንትነር) ለመቶ ኪሎ ይጠቀማል። በእስፓንያ centena /ሴንቴና/ በድሮው ትርጉሙ መቶ ፓውንድ ወይም 46 ኪሎ ማለት ነው፤ በጀርመን አገር Zentner /ጸንትነር/ ለ50 ኪሎ መደበኛ ሆኖአል፤ የመቶ ኪሎ መለኪያ በጀርመን አገር አሁን Doppelzentner /ዶፐልጸንትነር/ ይባላል።