Jump to content

ነቀን

ከውክፔዲያ
(ከሄራኮንፖሊስ የተዛወረ)
ህየራኮንፖሊስ
ነቀን
በነቀን የተገኘ የሸክላ አንበሳ ቅርጽ፣ 3000 ዓክልበ. ግድም
ህየራኮንፖሊስ is located in ግብፅ
{{{alt}}}
ህየራኮንፖሊስ

25°5′ ሰሜን ኬክሮስ እና 32°46′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


ነቀን (ግሪክኛ፦ Ιεράκων πόλις፤ /ህየራኮን ፖሊስ/ «የጭላት ከተማ») የጥንታዊ ግብፅ ከተማ ነበረ።

ከግብጽ ቀድሞ ዘመነ መንግሥት ወቅት አስቀድሞ የላይኛ ግብጽ ቤተ መንግሥት በነቀን ይገኝ ነበር፣ ይህ በአባይ ወንዝ ሸለቆ የነበሩት ሀገራት በአንድ የግብጽ መንግሥት ገና ሳይዋሀዱ ማለት ነው። ከዚሁ ዘመን (3100 ዓክልበ. ግድም) ብዙ ቅርሶች ለምሳሌ የጊንጥ ዱላ እና የናርመር መኳያ ሠሌዳ በነቀን ተገኝተዋል።

ከዚህ ዘመን በኋላ በመካከለኛው መንግሥት ደግሞ (2075 ዓክልበ. ግድም) የላይኛ ግብጽ 3ኛ ኖም መቀመጫ ሆኖ ነበር።