Jump to content

መንግሥት

ከውክፔዲያ
(ከመንግስት የተዛወረ)

መንግሥት በአንድ አገር ወይም ተቋም ውስጥ ሕጎችን ለማውጣትና ለማስፈጸም ስልጣን ያለው አካል ነው። መንግሥት አንድ ሃገር ወይም ማህበረሰብ የሚስተዳደርበት ሥርዓትና ለዚህም ሲባል የተቋቋመ ኃይል ያለው አካል ነው ፡፡ ይህም ህግ አውጪውን፣ ህግ አስፈጻሚውን እና ህግ ተርጓሚውን ማለትም የዳኝነት አካላትን የያዘ ነው፡፡

ድርጅቶች ሁሉ እንደ መንግሥት ያለ አስተዳደር ሲኖራቸው ፣ መንግሥት የሚለው ቃል በተለይ በግምት 200 የሚሆኑ አገራዊ መንግስታትን በበለጠ ያመለክታል፡፡

የመንግስት አመሠራረት መቼ እንደተጀመረ በእርግጠኝነት መናገር ይቸግራል ፡፡ ሆኖም ታሪክ የጥንታዊ መንግስታትን ምስረታ ይመዘግቧል ፡፡ ከ 5,000 ዓመታት በፊት የመጀመሪያዎቹ ትናንሽ የከተማ መንግስታት ብቅ ብቅ እንዳሉ ይገመታል ፡፡ ከሶስተኛው እስከ ሁለተኛው ዓመተ ዓለም ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ወደ ትልልቅ አካባቢዎች በማደግ እንደ ሱመርየጥንቷ ግብፅየኢንዲስ ሸለቆ ስልጣኔ እና ቢጫ ወንዝ ስልጣኔ የሚባሉትን ፈጥረዋል ።

ግብርና ልማት እና የውሃ ቁጥጥር ለመንግስት ማደግና መጠናከር እንደ ዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የአንዳንድ ነገድ አለቆች የእነሱን ጎሳ ለማስተዳደር በተለያዩ የአምልኮ ሥርዓቶች ወይም ባላቸው ጥንካሬ ተመርጠው አስተዳድረዋል፣ አንዳንዴም ከጎሣው ሽማግሌዎች ጋር በመሆን መንግሥት ሆነዋአል፡፡ በግብርና የበለጠ ውጤታማ እየሆኑ መሄድ በአንድ አካባቢ የሚኖረው ህዝብ ብዛቱ እንዲጨምር አስችሏል። ይህም ​​በተለያዩ ቡድኖች መካከል የሚደረጉ ግንኙነቶች እየጨመሩ እንዲሄዱና የሚፈጠረውንም መሥተጋብር የሚቆጣጠር አካል (መንግሥት) እንዲኖር አድርጓል።

እ.ኤ.አ. ከ 17 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ጀምሮ የሪፖብሊካዊ መንግስት ተስፋፍቷል፡፡ የእንግሊዝ፣ የአሜሪካና የፈረንሳይ አብዮቶች ለተወካይ የመንግስት ምሥረታ እድገት አስተዋጽኦ አበርክቷል ፡፡ የኮሚኒስት መንግስት የተመሠረተበት የመጀመሪያው ሠፊ ሀገር ሶቪዬት ህብረት ነው። የበርሊን ግንብ ከተደረመሰ ጊዜ ጀምሮ የሊበራል ዴሞክራሲ የተስፋፋ የመንግሥት መስተዳድር ሆኗል ።