Jump to content

ሲከሌውስ

ከውክፔዲያ
(ከሲኪሌውስ የተዛወረ)

ሲከሌውስእስፓንያ አፈ ታሪክ ዘንድ ከአባቱ ሲካኑስ በኋላ በኢቤሪያና (እስፓንያ) በሲኪሊያ ላይ ንጉሥ ነበር። ስሙን ለሲኪሊያ ደሴት እንደ ሰጠ ይጻፋል።

በሲኪሌውስ ዘመን በጣልያን አገር በኩል አንድ ጠብና ብሔራዊ ጦርነት በተነሣበት ጊዜ፣ ሲኪሌውስ ንጉሣቸውን ያሲዩስ ያኒጌናን በወንድሙ በዳርዳኑስና በጓደኛው በሮማነሦስ (የአቦሪጌኔስ አለቃ) ላይ ደገፈው። በ1758 ዓክልበ. ግድም ዳርዳኑስ ወንድሙን ያሲዩስን በተንኮል በቬቱሎኒያ ውግያ ገደለው፤ ወዲያው ግን ሲኪሌውስ ደርሶ ዳርዳኑስን ከጣልያን አባረረው። ዳርዳኑስም ወደ ሳሞትራቄ ሸሸ፣ ከጊዜ በኋላ በ1736 ዓክልበ. አካባቢ ይህ ዳርዳኑስ ትሮያንማዮንያ የመሠረተው ይባላል።

ሲኪሌውስ ዳርዳኑስን ከጣልያን ባባረረውበት ዓመት እርሱም ዓረፈ፤ ልጁም ሉሱስ በሂስፓንያ ዙፋን ተከተለው። በጣልያንም የያሲዩስ ልጅ ኮሪባንቱስ ተከተለው።

ቀዳሚው
ሲካኑስ (የሲኮሩስ ልጅ)
የሂስፓኒያ ንጉሥ (አፈታሪክ) ተከታይ
ሉሱስ