ስዕል:Public poem and war songs for the patriot Fitawurari Ayele Tessema.jpeg

ከውክፔዲያ

Public_poem_and_war_songs_for_the_patriot_Fitawurari_Ayele_Tessema.jpeg(405 × 574 ፒክስል፤ መጠን፦ 37 KB፤ የMIME ዓይነት፦ image/jpeg)

አየለ አባ ጓዴ ጥይቱ ብዙ እንደ ነጋዴ፡፡ አባት አስገዳይ ብለዉ ሲያሙት ወንድም አስገዳይ ብለዉ ሲያሙት ነጭ ሰዉ ገዳይ ወርዶ አማኒት፡፡ የሙላት አሽከር የቀስቅስ ወንድም ክብሪት ካልጫሩት እሳት አይነድም እንደ ላም ጥጃ ሳይዝ አይሄድም ለጣሊያን ጦር አይገደድም ለወደረኛዉ አይዋረድም፡፡ በአያቱ ብረት በአባቱ ብረት በወንድሙ ብረት የተደነቀ ሙያ ሰራበት፡፡ አማኒት በሩ የከበረዉ ላምባልጋ በሩ የተከበረዉ ቤዛሆ በሩ የተከበረዉ መተማ በሩ የተከበረዉ የቋራ በሩ የተከበረዉ በእነ አባ ጓዴ በማር ቤቶች ነዉ፡፡ የማር ቤቶች ልጀ የእነ አብዶ በላ ሲቸግር በእርሳስ ሲመች በዱላ፡፡ የአባ ሙላት ልጅ የባለ ሱሪ የቀስቅስ ወንድም የፊትአዉራሪ ከአዳራሻቸዉ አይበላም ፈሪ ራሱ የሚሄድ ምንሻ ገሪ ከጥይት ጥይት መርጦ ቀርቃሪ ንብ የመሰለ ባንዳ አባራሪ የተጠመደ መድፍ አዛዋሪ የአበዛል እንጅ አይባል ፈሪ፡፡ አማኒት ገዳይ ከደመናዉ ስር የኢጣሊን ጓንዴ ጉጉት ሲመስል ገዳይ አማኒት እንደ አራስ ነብር ተጉዞ ሌሊት፡፡ ገዳይ ኩመር በር በለዉ እያለ ከቀስቅስ ጋር፡፡ የአባቱን ጠላት የተሰማን የታዴን ጠላት የወንድሙን በቁሙ ጠጣዉ በሳንጃ አልቢን አርዶ በካር ጠጣዉ ደሙን፡፡ አዉጋ ላይ ገዳይ ከመቃጠሪያዉ አደዛ ላይ ገዳይ ከመዛወሪያዉ ጓንግ ላይ ገዳይ ከመናሃሪያዉ ያባ ሙላት ልጅ ልቡን ያመነዉ ተመልከት ብሎ ስቆ ገደለዉ እንደ ነሃሴ ጅኑ ከባድ ነዉ እንደ ሚካኤል መልኩ አማሪ ነዉ፡፡ ብሩ ሠፈር ገዳይ አስገዳይ ተራ በተራ ቤዛሆ ገዳይ ቆሣይ አስቆሳይ ከልጁ ጋር ከበብነዉ ብሎ ጠላት ሲያወራ መንጥሮት ወጣ ያን ትልቅ ስፍራ የተጨፈጨፈ የነጭ አዝመራ፡፡ የፈጣን ፤የመርዞ ፤የጨካኝ ፤የዉቃዉ ፤የጓዴ ብረት ፊት እየመራ በመረዳዳት ጭልጋና ናራ የመጣዉ ጠላት ገብቷል ሮማ በአየለ አመራር በአርበኞች ስራ፡፡ ለእናት ሀገሩ ያገለገለዉ የጦር ቀን ንጉስ የአለም ቀን ድሃዉ ትዉልዱን ጭልጋ ያላስደፈረዉ ልጅ ከወለዱ እንደ አባ ጓዴ ነዉ፡፡ ፊት አዉራሪ አየለ ድነጉር መደናገር ክፉ አይወጣዉ ከአፉ ሲቆርጥ አይታይም ሲወድቅ ነዉ ዛፉ፡፡ የመኪናዉ ብዛት የጦርም ብዛቱ ፊት አዉራሪ አየለ የተዋጋበቱ፡፡ አየለ አባ ጓዴ የደበደበዉ መልሶ አጨብጭቧል አማኒት ካንቻዉ፡፡ አየለ አባ ጓዴ ሰራቆ ተዋግተህ አማኒት ተዋግተህ ወይኒ ላይ ተዋግተህ አራስ ዉሻ ገለህ አገሩን አቅንተህ በነበረዉ መንግስት ተሹመህ ገዝተሃል ከእንግዲህስ ወዲያ ዳዊቱን ድገመዉ እሱዉ ይበቃሃል፡፡

Prepared and written by Ashu Wasie

የፋይሉ ታሪክ

የቀድሞው ዕትም ካለ ቀን/ሰዓቱን በመጫን መመልከት ይቻላል።

ቀን /ሰዓትናሙናክልሉ (በpixel)አቅራቢውማጠቃለያ
ያሁኑኑ18:42, 26 ኤፕሪል 2014በ18:42, 26 ኤፕሪል 2014 የነበረው ዕትም ናሙና405 × 574 (37 KB)Ashu wasie (ውይይት | አስተዋጽኦ)አየለ አባ ጓዴ ጥይቱ ብዙ እንደ ነጋዴ፡፡ አባት አስገዳይ ብለዉ ሲያሙት ወንድም አስገዳይ ብለዉ ሲያሙት ነጭ ሰዉ ገዳይ ወርዶ አማኒት፡፡ የሙላት አሽከር የ�...

የሚከተሉት 2 ፋይሎች የዚሁ ፋይል ቅጂዎች ናቸው፦

ወዲህ ፋይል የተያያዘ ገጽ የለም።

ተጨማሪ መረጃ