በርጊዮን

ከውክፔዲያ
(ከቤርጊዮን የተዛወረ)

በርጊዮን (ግሪክኛ፦ Βεργίων) ወይም ደርኩኖስ (Δέρκυνος) በጥንታዊ ግሪክ አፈ ታሪክ የፖሰይዶን ልጅና የአለቢዮን (አልቢዮን) ወንድም ሲሆን እርሱና አልቢዮን በሄራክሌስ ላይ ውግያ በሊጉርያ ተዋጉ። ይህ ሄራክሌስ የጌርዮን ከብት በኢቤሪያ (የእስፓንያ ልሳነምድር) ማርኮ ወደ ግሪክ አገር ሲመለስ ነበር ይባላል።[1]

በውግያው አልቢዮንና በርጊዮን ታላቅ ሠራዊት ነበራቸው፣ የሄራክሌስም ሠራዊት ሲቸገር ሄራክሌስ ለአባቱ (ዜውስ) ጸልዮ አሸነፈ፤ ሁለቱም ወንድማማች ተገደሉ።[2][3]

እንግላንድ አፈ ታሪካዊ ልማዶች ደግሞ ይህ በርጊዮን የአየርላንድና የኦርክኒ ደሴቶች ግዛት በአባቱ ኔፕቱን ወይም በአያቱ ኦሲሪስ ተሰጠ። ወንድሙም አልቢዮን ያንጊዜ በታላቅ ብሪታንያ ደሴት ይገዛ ነበር። በመጨረሻ ሄርኩሌስ ሊቢኩስ ሁለቱንም ወንድማማች በሮን ወንዝ በኩል በውግያ ገደላቸው።

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Schmitz, Leonhard (1867). William Smith, ed. Dictionary of Greek and Roman Biography and Mythology 1. Boston: Little, Brown and Company. p. 94. Archived from the original on 2011-06-04. Retrieved 2013-12-06. 
  2. ^ ቢብሊዮጤኬ ii. 5. § 10
  3. ^ ፖምፖኒዩስ ሜላ, ii. 5. § 39