Jump to content

የአራዳ ቋንቋ

ከውክፔዲያ
(ከአራድኛ ቃላት የተዛወረ)

(Yä 'Arada Q̣uwanq̣uwa) (Amharic Urban Youth Language) የአራዳ ቋንቋ በአማርኛና በማኅበራዊ አጋጣሚዎች ምክንያት አማርኛን በተጎራበቱ ቋንቋዎች የሚቀናበር ምርጥነትን፣ ሥልጡንነትን ለማሳየትና ከሌሎች ሰዎች ለመለየት የተፈጠረ በዋናነት የከተሜ ወጣቶች ቋንቋ ነው። የአራዳ ቋንቋ ተጠቃሚዎች ሌሎች "የእኛ ወገን ያልኾኑ" የሚሏቸው ሰዎች በአካባቢያቸው በሚኖሩበት ጊዜ ቋንቋውን ምሥጢር መለዋወጫ ሊያደርጉት ይችላሉ። የአራዳ ቋንቋን ለማቀናበር ተናጋሪዎቹ በዋናነት ግልበጣ፣ ጭመራ፣ ተውሶና ፍቺ ቅየራ፣ እንዲኹም ፈጠራን ይጠቀማሉ። የአራዳ ቋንቋ የአማርኛን ሥነ ድምፅ፣ ሥነ ምዕላድና ሥነ መዋቅር በጥብቅ ይከተላል። ምን ያኽል የቃላት ክምችት እንዳለው በትክክል ለመናገር ቢያስቸግርም የዕለት ተዕለት ጉዳዮች ላይ ያለምንም ችግር ተጠቃሚዎቹ ይገለገሉበታል።

  • አሪፍ፡- ጥሩ፣ ቆንጆ ነው።

ምሳሌ፡-ዛሬ አሪፍ ፊልም አየሁ። (ዛሬ ቆንጆ ፊልም አየሁ እንደማለት ነው።)

  • አብሽር - ጥሩ እንግዲህ
  • ሼም፡- አረ...የሚገርም ሰው ነው፤ ትንሽ እንኳ ሼም አየቆነጥጠውም!
  • ፀዳ ያለ፡- በጣም ጥሩ የሆነ

ትናንትና ፀዳ ያለ እራት ነው የበላሁት።

  • የገባው፡-

አቶ ቢመጣ እኮ ሽማግሌ አይመስሉም፤ የገባቸው ናቸው።

  • ጭሱ፡
  • ይመቻችሁ፡-

ፍሬንዶች አቦ ይመቻችሁ።

  • ፍንዳታ ፡ -አዲስ ብቅ የሚል ወጣት
  • እገሌ ሊጭር ነው፡ እገሌ ሊሞት ነው።
  • ይብራብኝ"--ይቅርብኝ ፣ይለፈኝ [ዛሬ ምሣ ይብራብኝ።]

"ወፍ የለም"--አይሆንም ፣ አይደረግም። እሱ ላይ እንዲህ አይነት ሳፋጣ ወፍ የለም።

ኧረ አይነፋም፡- ደስ አይልም፡ ኧረ አይነፋም ተው፡፡

ይብራብኝ፡- ይቅርብኝ፡ ይሄ ምግብ ለኔ ይብራብኝ፡፡


ጌጃ ...ሞኝ ዛፓ.....ፖሊስ


Mehari Worku. Arada: Sociolinguistic and Linguistic Features of the Amharic Urban Youth Language. (Addis Ababa University, 2012)