Jump to content

የአቅጣጫ ቁጥር

ከውክፔዲያ
(ከአቅጣጫ ቁጥር የተዛወረ)
የአቅጣጫ ቁጥር በጨረር ተመስሎ

የአቅጣጫ ቁጥር በእንግሊዝኛ Complex Number የሚባል ሲሆን የእንግሊዝኛው ስሙ ግን ስህተት ወይም የሚያምታታ ነው። የአቅጣጫ ቁጥሮች ሲጻፉ ባጠቃላይ መልኩ a+jb ወይም a+ib በሚል ሲገለጹ፣ a ና b የውን ቁጥር ሲሆኑ፣ i (በሂሳብ) ወይም j (ኤሌክትሪክ ምህንድስና ) ደግሞ ንጹህ የአቅጣጫ ቁጥር ናቸው፣ ዋጋቸውም ነው።

i ወይም j, ንጹህ የአቅጣጫ ቁጥር የተባሉበት ምክንያት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አድማሳዊ መስመር x ላይ ያለን ቁጥር በ1 ብናበዛው እዚያው መስመር ላይ፣ ያኑ ቁጥር እናገኛለን። ነገር ግን በ -1 ብናበዛ ያ ቁጥር በ180o ዲግሪ ይገለበጥና ተቃራኒውን ይሰጠናል። በ180o ለመገልበጥ ሁለት ጊዜ በ90o ዲግሪ መገልበጥ ስለሚያስፈልግ፣ ሁለት ጊዜ ተባዝቶ -1 የሚስጠን ስለሆነ፣ እንግዲይ ይህ ቁጥር ንጹህ የአቅጣጫ ቁጥር ነው ማለት ነው።