Jump to content

አቡካዶ

ከውክፔዲያ
(ከአቮካዶ የተዛወረ)
አቡካዶ

አቡካዶ (Persea americana) የዛፍ ዝርያና ከዚህ ዛፍ የመጣ ፍሬ ነው። የዛፉ መነሻ ከሜክሲኮ ነበር፤ ስያሜውም «አቡካዶ» (ወይም አቮካዶ ወይም ተመሳሳይ) ከናዋትል ስም «አዋካትል» ደረሰ። ፍሬውም በአበሳሰል የተወደደ ነው።

የሳይንስ ሊቃውንት እንደሚገልጹ፣ እጅግ ታላላቅ አራዊት በምድር ላይ በተመላለሱበት ዘመን፣ ፍሬው እንዲመግባቸው እንደ ተደረጀ ይመስላል። ታላቁም ዘር በፋጋቸው ውስጥ ስለ ተረፈ በነርሱ አማካኝነት ዛፉ ተስፋፍቶ በድሮ ከሜክሲኮ ውጭ በሰፊ እንደ ተገኘ ይላሉ።