Jump to content

ዔቦር

ከውክፔዲያ
(ከኤቦር የተዛወረ)
ኤቦር በ1545 ዓ.ም. ለሳለው ለጊዮም ሩዊ እንደ መሰለው

ዔቦር (ዕብራይስጥ፦ עֵבֶר /ዔበር/) በኦሪት ዘፍጥረት መሠረት የሳላ ልጅና የፋሌቅና የዮቅጣን አባት ነበረ።

ዘፍጥረት 11፡16-17 ስለ ዔቦር እንደሚለው፣ የዔቦር ዕድሜ 134 ዓመት ሲሆን ፋሌቅን ወለደ፣ ከዚያም ዔቦር 430 ዓመት ኖረ። 134 የሚለው ቁጥር ከግሪክና ሳምራዊው ትርጉሞች ጋር ሲስማማ፣ 430 የሚለው ቁጥር ግን ከዕብራይስጡ ተወስዷል። በዕብራይስጥ የወለደበት ዕድሜ 34 ዓመት ነው፤ በሳምራዊውም ትርጉም ከዚያ ለ270 ዓመታት ኖረ፣ በግሪኩም ከዚያ ለ370 ዓመታት ኖረ።

መጽሐፈ ኩፋሌ 8፡39 ኤቦር ከአባቱ ሳላና ከእናቱ ሙአክ በ1503 አመተ አለም ተወለደ። በ1564 አ.አ. ሚስቱን አዙራድ አገባ፤ እርሷም የአብሮድ ወይም የነብሮድ (ናምሩድ) ልጅ ትባላለች። በ1567 አ.አ. አዙራድ ልጁን ፋሌቅን ወለደችለት ይላል።

ከቅዱሳን መጻሕፍት ውጭ ባሉት አይሁዳዊ ልማዶች ዘንድ፣ ዔቦር የባቢሎን ግንብ በትሰራበት ወቅት ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልነበረም። ስለዚህ በኋላ ልሳናቱ ሁሉ ተደበልቀው ዔቦር ብቻ መጀመርያውን (የአዳም) ቋንቋ ጠበቀ። አንዳንድ ጸሐፊ እንደሚያምን ዕብራውያን ስማቸውን ከዔቦር ተቀበሉ። (በሌላ አስተሳስብ ግን ስማቸው ከኤቦር ሳይሆን በኋላ ኤፍራጥስ ወንዝን ከአብራም ጋር ስለተሻገሩ 'ተሻጋሪዎች' ማለት እንደሆነ ይባላል።)

ጀርመን ታሪክ ጸሐፊ ዮሐንስ አቬንቲኑስ 1513 ዓ.ም. ባሳተመው መዝገቦች ዘንድ፣ አሕዛብ ከሰናዖር ከተበተኑ በኋላ ሳላ ከአባቱ ሳላና ከልጁ ኢስተር (ዮቅጣን) ጋራ በአሁኑ ኦስትሪያ ዙሪያ ሠፈረ። ዔቦር ከሠራቸው ከተሞች መካከል ኤበርስበርግኤበርስሃውዘን እንዲሁም ስቶከራው ይጠቅሳሉ። የዔቦር ዕድሜ 464 አመት ሲሆን እንዳረፈ ይጨምራል።