አገውምድር

ከውክፔዲያ
(ከእንጅባራ የተዛወረ)
Jump to navigation Jump to search
እንጅባራ
Injibara town.jpg
እንጅባራ ከተማ (ኮሶበር)
ከፍታ 2,560 ሜትር
እንጅባራ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
እንጅባራ

10°57′ ሰሜን ኬክሮስ እና 36°56′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

ምርጧ ከተማ 

እንጅባራባንጃ ወረዳ የሚገኝ ከተማ ሲሆን የአገው አዊ ዞን አስተዳደር ማዕከል ነው። የከተማው አቀማመጥ በተራሮች መካከል ሲሆን በተለይ ከአለት የበቀለው የለዊ እና ዚሪሂ ተራራ የከተማው ልዩ መታወቂያ ነው። የእንጅባራ ከተማ የምትገኘው በሰሜን ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጎጃም አዊ ዞን ከአዲስ አበባ በ447 ኪ.ሜ. ከክልሉ መንግሥት መቀመጫ ከሆነችው ባህርዳር ከተማ ደግሞ 122 ኪ.ሜ.፣ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋም በ 10º 53’ ሰሜን ላቲቲውድ እና 36º 56’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡ እንጅባራ ከተማ ከአዲስ አበባ ባህርዳር ዋና መንገድ ላይ የምትገኝ ሲሆን ወደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚወስደው መንገድም በከተማዋ ያልፋል::

አመሰራረት

እንጅባራ ከተማ የተቆረቆረችው በ1884 ዓ.ም. ነው፡፡

በከፍተኛ ፍጥነትም እያደገች ያለች ከተማ ነች::

የከተማ ማኔጅመንትና ፕላን

እንጅባራ በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንዷ ስትሆን፣ የከተማ አስተዳደር፣ ማዘጋጃ ቤት፣ 5 የከተማና 1 የገጠር ቀበሌዎች አላት፡፡ በ2003 ዓ.ም የተዘጋጀ መዋቅራዊ ፕላንም አላት፡፡


ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]