ስዋሂሊ
Appearance
(ከኪስዋሂሊ የተዛወረ)
ስዋሂሊ ፡ (ወይም ፡ ኪሷሂሊ Kiswahili) ፡ በምሥራቅ ፡ ፡ የሚናገር ፡ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። (፭ ፡ ሚሊዮን ፡ ተናጋሪዎች) ፡ ልደት ፡ ቋንቋ ፡ ከመሆኑ ፡ በላይ ፡ ለ ፴ ፡ እስከ ፡ ፶ ፡ ሚሊዮን ፡ ሌሎች ፡ ሰዎች ፡ ሁለተኛ ፡ ቋንቋ ፡ ሆኗል። የስዋሂሊ ፡ ስም ፡ መነሻ ፡ ከ ፡ ቃል ፡ «ሰዋሂል» ፡ ነበር ፤ ይህም ፡ የ«ሳኸል» ፡ (ማለት ፡ ዳር) ፡ ብዙ ፡ ቁጥር ፡ ነው። ስለዚህ ፡ የ«ስዋሂሊ» ፡ ትርጉም ፡ የ(ባሕር) ፡ ዳረኞች ፡ ቋንቋ ፡ ሊሆን ፡ ይችላል። የቋንቋው ፡ ቤተሰብ ፡ ባንቱ ፡ ሲሆን ፡ ተናጋሪዎቹ ፡ መርከበኞችና ፡ ነጋዴዎች ፡ በመሆናቸው ፡ መጠን ፡ ከዓረብኛ ፣ ከ ፣ ከ ፣ እና ፡ ከ ፡ ቢሆንም ፡ ብዙ ፡ ቃሎች ፡ ተበድረዋል።
- mtoto mmoja anasoma - «ምቶቶ ፡ ምሞጃ ፡ አናሶማ» - አንድ ፡ ልጅ ፡ ያነብባል።
- watoto wawili wanasoma - «ዋቶቶ ፡ ዋዊሊ ፡ ዋናሶማ» - ሁለት ፡ ልጆች ፡ ያነብባሉ።
- kitabu kimoja kinatosha - «ኪታቡ ፡ ኪሞጃ ፡ ኪናቶሻ» - አንድ ፡ መጽሐፍ ፡ ይበቃል።
- vitabu viwili vinatosha - «ቪታቡ ፡ ቪዊሊ ፡ ቪናቶሻ» - ሁለት ፡ መጻሕፍት ፡ ይበቃሉ።
- ndizi moja inatosha - «ንዲዚ ፡ ሞጃ ፡ ኢናቶሻ» - አንድ ፡ ሙዝ ፡ ይበቃል።
- ndizi mbili zinatosha - «ንዲዚ ፡ ምቢሊ ፡ ዚናቶሻ» - ሁለት ፡ ሙዝ ፡ ይበቃሉ።
- Kamusi Project Archived ጁን 20, 2012 at the Wayback Machine Internet Living Swahili Dictionary