ሥነ-እንቅስቃሴ
Appearance
(ከየእንቅስቃሴ ህግጋት የተዛወረ)
ሥነ-እንቅስቃሴ (mechanics) የሚባለው የፊዚክስ ጥናት ቁስ ነገሮች የጉልበት ግፊት ወይም ስበት ሲደረግባቸው ወይንም ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ በከባቢያቸው ቁስ ላይ ምን አይነት ለውጥ ያመጣሉ ብሎ የሚያጠና የሳይንስ ዘርፍ ነው። ይህ የጥናት ዘርፍ ለስነ-ተፈጥሮ ትምህርት መሰርታዊ ከመሆኑ የተነሳ ከጥንት ዘመን ጀመሮ ሲጠና ኖሩዋል። በአሁኑ ጊዜ፣ ዘርፉ በዘመናት ሂድት ካካበተው የጎለመሰ ዕውቀት የተነሳ ብዙ የጥናት ዘርፎችን አካቶ ይዞ ይገኛል። ሆኖም ግን በእለት ተእለት በሚያጋጥሙን ቁሶች ዘንድ የሚካሄደውን የቁሶች ባህርይ በሚገባ የሚያስረዳው የሥነ-እንቅስቃሴ ዘርፍ በ16ኛው ክፍለ ዘመን በነበረው እንግሊዛዊ ኢሳቅ ኒውተን በሚገባ ተጠቃሎ ቀርቦአል። ምንም እንኳ ኢሳቅ ኒውተን ህጎቹን በራሱ ባያገኛቸውም፣ እሱ ግን በሚገባ በመፈረጅና ጥቅማቸውንም ጥራዝ ነጠቅ ባልሆነ መልኩ እንዴት እንደሚሰሩ በማሳየት አስገንዝቦ አልፎአል። በተለምዶ የኒውተን ህግ ተብለው የሚታወቁት 3ቱ የስነ-እንቅስቃሴ ህጎች እንሆ፦
የእንቅስቃሴ ህጎች | |
---|---|
የመጀመሪያው የእንቅስቃሴ ህግ | ማንኛውም ነገር (ቁስ) የተጣፋ ጉልበት ወይም ምንም ጉልበት እስካረፈበት ድረስ ባለበት ፍጥነት (በቀጥታ መስመር) ይቀጥላል -- የቆመውም በቆመበት፣ 10ሜትር በሰከንድ የሚጓዘውም በዚያው ፍጥነት በቀጥታ መሰመር። |
ሁለተኛው የእንቅስቃሴ ህግ | ማንኛውም ነገር (ቁስ) ያልተጣፋ ጉልበት ጉ ካረፈበት፣ ባረፈበት ጉልበት አቅጣጫ ፍጥነቱን ይጨምራል። ይህም ፍጥንጥነት ፍ (acceleration) የቁሱ ክብደት ክ ከተለቀ ያንሳል፣ ክብደቱ ካነሰ ደግሞ ይበዛል፣ ነገር ግን ጉልበቱ ከበዛ ይበዛል ጉልበቱ ካነሰ ያንስል። ይህን በሂሳብ ቀመር ስንፅፈው ጉ =ክ X ፍ |
ሶስተኛው የንቅስቃሴ ህግ | ሁለት ቁሶች ሲነካኩ አንዱ አንደኛው ላይ የሚይሳርፈው ጉልበት መጠናቸው አንድ ሆኖ ግን አቅጣጫቸው በተቃራኒ መስመር ነው። |
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |